የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሁለተኛ ዙር የመጀመርያ ጨዋታዎች በሳምንቱ መጨረሻ ይከናወናሉ። ቅዳሜ ሁለት ጨዋታዎች እሁድ ደግሞ ቀሪዎቹ ስድስት ጨዋታዎች እንደሚካሄዱ ለማወቅ ተችሏል።
አንድ የሜዳው ጨዋታ የተቀጣው ፋሲል ከነማ ባህር ዳር ላይ ከአዳማ ከተማ ጨዋታውን የሚያከናውን ሲሆን ባህር ዳር ከተማ እሁድ ጨዋታውን የሚያከናውን በመሆኑ ነው ፋሲል ቅዳሜ ጨዋታውን የሚያደርገው። በተመሳሳይ ቅዳሜ በ10፡00 ኢትዮጵያ ቡና በሜዳው ስሑል ሽረን ያስተናግዳል።
እሁድ ቀሪዎቹ የ16ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ቀጥለው ሲካሄዱ የሜዳ ቅጣቱን የጨረሰው ሀዲያ ሆሳዕና በሜዳው አቢዮ ኤርሳሞ መቐለ 70 እንደርታን ሲያስተናግድ ወልዋሎም በታደሰው ሜዳው ዓዲግራት ላይ ሰበታ ከተማን ይገጥማል። ቅዱስ ጊዮርጊስ ደግሞ በ10:00 ወልቂጤ ከተማን ያስተናግዳል። ሌሎቹ ጨዋታዎች በተለመዱት ሰዓት እና ቦታዎች እንደሚከናወኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
በመርሐ ግብር ላይ ያሉ ለውጦች እና አዳዲስ ጉዳዮችን ተከታትለን እናቀርባለን።
16ኛ ሳምንት | ||
ቅዳሜ የካቲት 28 ቀን 2012 | ||
ፋሲል ከነማ | 9:00 | አዳማ ከተማ |
ኢትዮጵያ ቡና | 10:00 | ስሑል ሽረ |
እሁድ የካቲት 29 ቀን 2012 | ||
ሀዲያ ሆሳዕና | 9:00 | መቐለ 70 እንደርታ |
ሲዳማ ቡና | 9:00 | ወላይታ ድቻ |
ወልዋሎ ዓ/ዩ | 9:00 | ሰበታ ከተማ |
ባህር ዳር ከተማ | 9:00 | ጅማ አባ ጅፋር |
ድሬዳዋ ከተማ | 9:00 | ሀዋሳ ከተማ |
ቅዱስ ጊዮርጊስ | 10:00 | ወልቂጤ ከተማ |
© ሶከር ኢትዮጵያ