መሐመድ ናስር ወደ ወላይታ ድቻ አምርቷል

ከሀዲያ ሆሳዕና ጋር ከወራት በፊት የተለያየው አንጋፋው አጥቂ መሐመድ ናስር ወደ ወላይታ ድቻ አምርቷል።

መስከረም ወር ላይ ሀዲያ ሆሳዕናን ተቀላቅሎ የነበረው መሐመድ ናስር ብዙም ሳይቆይ ከክለቡ ጋር በስምምነት በመለያየት የጦና ንቦቹን በአንድ ዓመት የውል ጊዜ ፊርማውን አኑሯል፡፡ ለበርካታ የፕሪምየር ሊግ ክለቦች የተጫወተው መሐመድ በባዬ ገዛኸኝ ላይ ጥገኛ ለነበረው የፊት መስመሩ አማራጭ እንደሚሆን ሲጠበቅ ከቀናት በፊህ ከክለቡ ጋር የተለያየው ሳምሶን ቆልቻን ቦታ ይሸፍናል ተብሎ ይጠበቃል።

© ሶከር ኢትዮጵያ