የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛው ዙር ግምገማ በቀጣዩ ሳምንት ቅዳሜ የሚደረግ ሲሆን መጋቢት 23 ደግሞ ሁለተኛው ዙር ይጀመራል፡፡
አስራ አንድ ክለቦችን ተካፋይ የሚያደርገው የ2012 የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪምየር ሊግ አንደኛ ዲቪዚዮን ውድድር የፊታችን ዕሁድ በሚደረግ አንድ ቀሪ ጨዋታ የመጀመሪያውን ዙር ያጠናቀቃል፡፡ ይህንንም ተከትሎ በአንደኛው ዙር የነበሩት አጠቃላይ ደካማ እና ጠንካራ ጎን ጨምሮ የውድድሩ ሙሉ ሒደት የሚገመግም የውይይት መድረክ በቀጣዩ ሳምንት ቅዳሜ መጋቢት 12 ከ3:00 ጀምሮ በኢትዮጵያ ሆቴል የክለብ ተወካዮች በመገኘት እንደሚያካሂዱ የሴቶች ልማት ኮሚቴ እና ውድድር ዳይሬክቶሬት ለክለቦች በላከው ደብዳቤ ገልጿል፡፡
በተያያዘም የአንደኛ ዲቪዚዮን የፕሪምየር ሊግ ውድድር ሁለተኛው ዙር መጋቢት 23 የሚጀመር ሲሆን አስር ክለቦችን ተሳታፊ የሚያደርገው የሁለተኛ ዲቪዚዮን ሁለተኛ ዙር መጋቢት 19 እንደሚጀምር ከፌዴሬሽኑ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡
© ሶከር ኢትዮጵያ