አፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ | ዝሆኖቹ አዲስ አሰልጣኝ ቀጥረዋል

በአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ከኢትዮጵያ ጋር ተደልድላ ጨዋታዎቿን በማድረግ ላይ የምትገኝነው አይቮሪኮስት የቀድሞ ረዳት አሰልጣኟ ፓትሪስ ቡዋሜሌን አዲስ አሰልጣኝ አድርጋ ቀጥራለች።

የአፍሪካ ዋንጫ ማጣርያ ጨዋታዎች በሀገራቸው አሰልጣኝ ኢብራሂም ካማራ እየተመሩ ጨዋታዎቻቸው በማድረግ የቆዩት ዝሆኖቹ አሰልጣኙን ያሰናበቱ ሲሆን በ2015 ዝሆኖቹ የአህጉሪቱን ዋንጫ ሲያነሱ የሄርቨ ሬናርድ ምክትል ሆኖ የሰራው የአርባ አንድ ዓመቱ ፈረንሳዊ አሰልጣኝን ምርጫቸው አድርገዋል።

በ2013/14 የዛምቢያ ብሔራዊ ቡድንን በዋና አሰልጣኝነት የመራው አሰልጣኙ በሞሮኮ እና በፈረንሳዩ ክለብ ሊል በሄርቬ ሬናርድ ስር በምክትልነት ሲያገለግል ቆይቷል። ከስድስት ዓመታት በኋላም ወደ ዋና አሰልጣኝነት ቦታ ተመልሶ ዝሆኖቹን ወደ አፍሪካ ዋንጫ የማሳለፍ ሀላፊነት ተረክቧል።

ከሳምንታት በኃላ ማዳጋስካርን የሚገጥሙት አይቮሪኮስቶች በ2021 ኦገስት 31 ኢትዮጵያን በሜዳቸው ይገጥማሉ።

© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ