ያሬድ ዘውድነህ ከብርቱካናማዎቹ ጋር ለተጨማሪ ዓመት ውሉን አራዝሟል

በሁለተኛው ዙር ራሳቸውን አጠናክረው ለመቅረብ ጥረት እያደረጉ ያሉት ድሬዳዋ ከነማዎች አዲስ ተጫዋች በማስፈረም እና ውል በማራዘም ላይ ይገኛሉ። ከዚህ ቀደም የአማካዩ ኤልያስ ማሞን ውል ማራዘማቸው የሚታወስ ሲሆን ዛሬ ደግሞ የተከላካይ መስመር ተጫዋቹ ያሬድ ዘውድነህን ውል አራዝመዋል።

ሁለገብ የተከላካይ ስፍራ ተጫዋች የሆነው ያሬድ ባለፈው የውድድር ዓመት አጋማሽ ላይ ወደ ድሬዳዋ ከተማ ተመልሶ እየተጫወተ የሚገኝ ሲሆን ዘንድሮ በመቅዶኒያ ሙከራ አግኝት የነበረ ቢሆንም የአውሮፓ የዝውውር መስኮት በመዘጋቱ ምክኒያት መጓዝ እንዳልቻለ የሚታወስ ነው። በክረምቱ የዝውውር መስኮትም ወደ መቅዶኒያ እና ወደ ጃፓን የሙከራ ጊዜ እንደሚኖረው ወኪሉ ቴዎድሮስ ከፈነ ለሶከር ኢትዮጵያ ገልጿል።

ከዚህ ቀደም በዳሽን ቢራ፣ ጅማ አባ ጅፋር እና ወልዲያ የተጫወተው ያሬድ ለተሰላፊነት ከአዳዲስ እና ነባር ተጫዋቾች ፉክክር ይጠብቀዋል።

©ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ