የዮናስ በርታ ማረፍያ ወልዋሎ መሆኑ ተረጋግጧል

በትናንትናው ዕለት በርካታ ተጫዋቾች ያስፈረሙት ወልዋሎዎች አማካዩ ዮናስ በርታን አስፈርመዋል።

ባለፈው ክረምት ደቡብ ፖሊስን ለቆ ወደ አዳማ ከተማ ካመራ በኃላ የመሰለፍ ዕድል ባለማግኘቱ ከክለቡ ጋር በስምምነት የተለያየው ይህ የቀድሞ የባህር ዳር ከተማ አማካይ ከበርካታ አማካዮቻቸው ጋር ለተለያዩት ወልዋሎዎች ጥሩ ፊርማ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል። ወደ ወልዋሎ ከማምራቱ በፊት ከበርካታ ክለቦች ጋር ስሙ ሲነሳ የቆየው ይህ አማካይ ባለፈው ዓመት በአሰልጣኝ አብርሀም መብራቱ ጥሪ ተደርጎለት ወደ ብሄራዊ ቡድኑ ማምራቱ ይታወሳል።

በቀጣይ እሁድ በሜዳቸው ሰበታ ከተማን የሚገጥሙት ወልዋሎዎች ቡድናቸውን ለማጠናከር ተጨማሪ ዝውውሮች ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

© ሶከር ኢትዮጵያ