ስሑል ሽረዎች የተከላካያቸውን ውል አራዝመዋል

ተከላካዩ ዮናስ ግርማይ ለቀጣዩ አንድ ዓመት ከቡድኑ ጋር ለመቆየት ውሉን አራዝሟል።

ባለፈው የውድድር ዓመት አጋማሽ ከመቐለ 70 እንደርታ ወደ ስሑል ሽረ በማምራት ቡድኑ በፕሪምየር ሊጉ እንዲቆይ ከፍተኛ ድርሻ የነበረው ዮናስ በጉዳት እና ቅጣት ካልተሰለፈባቸው ጨዋታዎች በስተቀር በሁሉም ጨዋታዎች ቡድኑን ያገለገለ ሲሆን በተለይም ከጋናዊው ተከላካይ አዳም ማሳላቺ ጋር የፈጠረው ጥምረት ለቡድኑ ተከላካይ ክፍል መሻሻል አይነተኛ ሚና ነበረው።

ከዚህ ቀደም ለትራንስ ኢትዮጵያ፣ ሰበታ ከተማ፣ ዳሽን ቢራ እና መቐለ 70 እንደርታ መጫወት የቻለው ዮናስ ግርማይ በርካታ ጨዋታዎች ቡድኑን በአምበልነት መምራቱም ይታወሳል።

©ሶከር ኢትዮጵያ