እንዳለ ከበደ እና መቐለ በስምምነት ተለያዩ

የመቐለ 70 እንርታው የመስመር አጥቂ እንዳለ ከበደ ከክለቡ በጋራ ስምምነት ተለያይቷል፡፡

የቀድሞ የአርባ ምንጭ ከተማ እና ሲዳማ ቡና ተጫዋች በ2011 የውድድር ዘመን ክረምት ወደ መቐለ አምርቶ ዓምና ከክለቡ ጋር የሊጉን ዋንጫ ያሳካው ይህ ተጫዋች ዘንድሮ እምብዛም የመሰለፍ ዕድል ያላገኘ ሲሆን ይህን ተከትሎ የተሻለ የመሰለፍ ዕድል ወደሚያገኝበት ክለብ ለማምራት የስድስት ወራት ቀሪ የቆይታ ጊዜ እየቀረው በጋራ ስምምነት ተለያይቷል፡፡

ከተለያዩ ክለቦች ጋር ስሙ እየተነሳ ያለው ባለ ክህሎቱ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች ከሰሞኑ አንድ የፕሪምየር ሊግ ክለብን እንደሚቀላቀል ይጠበቃል፡፡

©ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ