ስሑል ሽረ የመስመር ተጫዋች አስፈርሟል

በዝውውር መስኮቱ ዝምታን መርጠው ከነበሩት ክለቦች ውስጥ የነበሩት ስሑል ሽረዎች የግራ መስመር ተጫዋቹ ዮናታን ከበደን በማስፈረም ወደ ዝውውር ገብተዋል።

በመጀመርያው ዙር ከዓብዱለጢፍ መሐመድ ውጭ በግራ መስመር አማራጭ ያልነበራቸው ሽረዎች ዮናታንን ማስፈረማቸው ተከትሎ በቦታው የነበራቸው አማራጭ ያሰፋላቸዋል። ከዚ ቀደም ለዋናው ብሔራዊ ቡድን ጨምሮ በወላይታ ድቻ፣ ሀዋሳ ከተማ፣ አዳማ ከተማ፣ ኤሌክትሪክ እና አርባምንጭ ከተማ የተጫወተው ዮናታን ዓምና ከድሬዳዋ ከተማ ጋር ከተለያየ በኋላ በዝውውር መስኮቱ የስሑል ሽረ የመጀመርያ ፈራሚ በመሆን ወደ ሊጉ ተመልሷል።

በተያያዘ ዜና ከአሰልጣኝ ሳምሶን አየለ ጋር በስምምነት የተለያዩት ስሑል ሽረዎች በሁለቱ ወጣት አሰልጣኞች በረከት ገብረመድኅን እና መብራህቶም ፍስሀ እየተመሩ ኢትዮጵያ ቡናን ይገጥማሉ።

© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ