ወልቂጤ ጋናዊ አማካይ ተጫዋች አስፈረመ

የሁለተኛ ዙር ውድድር ዝግጅታችውን በአዲስ አበባ ከተማ እያደረጉ የሚገኙት ወልቂጤዎች ጋናዊው አሮን አሞሃን የግላቸው ማድረግ ችለዋል።

አሮን አሞሀ ለኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አዲስ ያልሆነ ተጫዋች ሲሆን የ2010 ፕሪምየር ሊግ ቻምፒዮን በሆነው ጅማ አባ ጅፋር ስብስብ መጫወት ችሎ የነበረ ሲሆን በዓመቱ መጨረሻ ወደ ሀገሩ ተመልሶ ከአንድ ዓመት ከግማሽ በኋላ ወልቂጤን በመቀላቀል ወደ ኢትዮጵያ መመለስ ችሏል።

አሮን በጋና ብሔራዊ ቡድን 17 እና 20 ዓመት በታች መጫወት የቻለ ሲሆን በሀገሩ ቡድን ጄትስ ተጫውቷል። በመሐል አማካይ እና አጥቂ ስፍራ ላይ የሚጫወቸው አሞሀ ከሀገሩ ልጅ ልሀሰን ኑሁ በመቀጠል ሁለተኛው የወልቂጤ ፈራሚ ሲሆን ለተሰላፊነት ከበርካታ ተጫዋቾች ፉክክር ይጠብቀዋል።

©ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ