ስሑል ሽረ አዲስ አሰልጣኝ ቀጠረ

በዚህ ሳምንት ከአሰልጣኝ ሳምሶን አየለ ጋር በስምምነት የተለያዩት ስሑል ሽረዎች ሲሳይ አብርሀምን አዲስ አሰልጣኝ አድርገዋል።

ከዚህ በፊት በአክሱም ከተማ፣ አዳማ ከተማ፣ ሼር ኢትዮጵያ እና የኢትዮጵያ ታዳጊ ብሄራዊ ቡድን ያሰለጠኑት አዲሱ አሰልጣኝ ባለፈው ዓመት በዚህ ወቅት ከአዳማ ከተማ ጋር በስምምነት ከተለያዩ ከአንድ ዓመት ቆይታ በኋላ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ክለብ ሥራ የሚመለሱ ይሆናል።

ቀደም ብለው ዮናታን ከበደን ያስፈረሙት ስሑል ሽረዎች በአጥቂው ሳሊፍ ፎፋና ምትክ አጥቂ ያስፈርማሉ ተብሎ ይጠበቃል።

©ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ