አዲስ ነጋሽ እገዳው ወደ 8 ወራት ዝቅ ተደረገለት

 

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን በቅርቡ ባስተላለፋቸው ውሳኔዎች ላይ ይግባኝ ለጠየቁ አካላት ምላሽ ሰጥቷል፡፡ በዚህም መሰረት አዲስ ነጋሽ እገዳው ዝቅ ሲደረግለት በአርቢቴር ጌቱ ተፈራ እና ረዳቶቹ ላይ ተላልፎ የነበረወ ውየ6 ወራት እገዳ ተሽሯል፡፡

ፌዴሬሽኑ ለሚድያ አካላት የላከው ፅሁፍ የሚከተለው ነው:-

*በኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ይግባኝ ሰሚ ኮሚቴ ጥር 25 እና የካቲት 1 /2008 ያስተላለፋቸው ውሳኔዎች

1. ታህሳስ 4 ቀን 2008 የቅዱስ ጊዮርጊስና ደደቢት የሴቶች እግር ኳስ ክለቦች በተጫወቱበት ወቅት ዋና ዳኛዋን ተማትታለች በማለት የቅዱስ ጊዮርጊስ ተጨዋች በሆነችው አትክልት አሸናፊ ላይ በዲሲፕሊን ኮሚቴ የተላለፈው የስድስት ወራት የጨዋታና የብር 5000 የቅጣት ውሳኔ ፀንቷል፡፡

2. ታህሳስ 21 ቀን 2008 ዓ.ም በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ እግር ኳስ ውድድር ዳሸን ቢራ እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ክለቦች በተጫወቱበት ወቅት ኤሌክትሪክ ተጨዋች የሆነው አዲሱ ነጋሽ ዋና ዳኛውን በቦክስ በመማታቱና ምራቁንም ዳኛው ላይ በመትፋቱ በዲስፕሊን ኮሚቴ የተላላፈበት የብር 5000 የገንዘብ ቅጣት ጸንቷል፡፡ የአንድ ዓመት የቅጣት እገዳ ደግሞ ወደ ስምንት ወራት ዝቅ እንዲል ተደርጓል፡፡

*የኤሌክትሪክ ተጨዋች የሆነው አማረ በቀለ አራተኛ ዳኛውንና ታዛቢውን በመሳደቡ በዲስፕሊን ኮሚቴ የተላላፈበት የአራት ጨዋታ ቅጣት ጸንቷል፡፡

*የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አሰልጣኝ የሆነው ብርሃኑ ባዩ ዋና ዳኛውንና ፌዴሬሽኑን ጸያፍ ስድብ በመሳደቡ በዲስፕሊን ኮሚቴ የተላለፈበት የ10 ጨዋታ ቅጣት እና የብር 5000 የገንዘብ ቅጣት ጸንቷል፡፡

ክለቦቹ ለይግባኝ ያስያዙት ገንዘብም ለፌዴሬሽኑ ገቢ እንዲሆን ተወስኗል፡፡

3. ታህሳስ 11 ቀን 2008 ዓ.ም በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የድሬዳዋ ከተማ እና ሃዲያ ሆሳዕና ክለቦች ካካሄዱት ጨዋታ ዳኝነት ጋር በተያያዘ ብሄራዊ የዳኞች ኮሜቴ በኮሚሽነር አሰፋ ንጉሴ ፣ በዋና ዳኛ ጌቱ ተፈራ እንዲሁም በረዳት ዳኛ ዳንኤል ዘለቀ ላይ ያስተላለፈው የስድስት ወራት የእገዳ ቅጣት ተሽሯል፡፡

 

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *