የአሰልጣኞች አስተያየት | ኢትዮጵያ ቡና 6-1 ስሁል ሽረ

በሁለተኛው ዙር የመጀመሪያ የጨዋታ ሳምንት ኢትዮጵያ ቡና አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ ስሑል ሽረን አስተናግዶ 6-1 ካሸነፈበት ጨዋታ መጠናቀቅ በኋላ የኢትዮጵያ ቡናው አሰልጣኝ ካሳዬ አራጌ ተከታዩን ሀሳብ ሰጥተዋል።

“ጨዋታው ከውጤት አንፃር ጥሩ ነው” ካሳዬ አራጌ (ኢትዮጵያ ቡና)

ስለ ጨዋታው

” ጨዋታው ከውጤት አንፃር ጥሩ ነው ፤ ብዙ ጎሎችን ማስቆጠር ችለናል። ነገር ግን በቀላሉ አንዳንድ እንቅስቃሴው ሊቀጥልባቸው የሚችሉ ኳሶች በቀላሉ ይበላሹ ነበር። ነፃ ቦታዎች ላይ ኳሱን በደንብ እንቆጣጠር ነበር፤ ነገርግን አንዳንዴ የተጋጣሚ ተጫዋቾች በበዛባቸው አካባቢዎች ኳሱን መቆጣጠር እየቻልን በቀላሉ ኳሶች ይበላሹ ነበር።”

ስለ ሁለተኛው ዙር ከቡድኑ ስለሚጠበቀው ነገር

“በመሰረቱ በአንደኛውና በሁለተኛው ዙር መካከል የ15 ቀን ልዩነት ነው ያለው። ያን ያህል የዓመታት ልዩነት የለም። በመጀመሪያው ዙር ላይ ከጨዋታ ጨዋታ እንደምናደርገው በተለይ ሒደቱ ላይ ያሉ ጨዋታውን ከተቆጣጠርን ማሸነፍ እንችላለን የሚል እምነት ስላለን በዛ ውስጥ የሚታዩትን ስህተቶች እያረምን ለመሄድ እንሞክራለን።”

* በስሑል ሽረዎች በኩል ሁለቱ ምክትል አሰልጣኞች ሀሳባቸውን ለመስጠት በማንገራገራቸው ማካተት ሳንችል ቀርተናል።

© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ