ስሑል ሽረ ጋናዊ የፊት መስመር ተጫዋች አስፈርሟል

ሳሊፍ ፎፈናን ያጡት ሽረዎች ራሂም ኡስማኖ የተባለ ጋናዊ አጥቂ አስፈርመዋል፡፡

ባለፉት ዓመታት በዛምቢያ ክለቦች ውስጥ በመጫወት የእግር ኳስ ህይወቱን ያሳለፈው ይህ ግዙፍ ተጫዋች በቡይልድ ኮን፣ ሙፍሪራ ወንድረርስ እና ዜስኮ ዩናይትድ የተጫወተ ሲሆን ዘንድሮ በጥር ወር ወደ አልጀሪያው ኤስኦ ችሌፍ ተዛውውሮ የነበረ ቢሆንም ምክንያቱ ባልታወቀ ምክንያት ተለያይቶ ወደ ኢትዮጵያ በመምጣት የሁለተኛ ዙር የመጀመሪያ የውጪ ዜጋ ፈራሚ በመሆን ቡድኑን በይፋ መቀላቀል ችሏል፡፡

የተጫዋቹ መፈረም ሳሊፍ ፎፋና ወደ ሀዲያ ሆሳዕና በማምራቱ የተፈጠረውን ክፍተት ይደፍናል ተብሎ ይጠበቃል።

© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ