ባህር ዳር ከተማ የመጀመሪያ ተጨዋቹን ለማስፈረም ተቃርቧል

የጣና ሞገዶቹ የመስመር አጥቂ ለማስፈረም ተቃርበዋል

በሊጉ ጥሩ ግስጋሴን እያደረገ የሚገኘው ባህር ዳር ከተማ በተጨዋቾች ጉዳት እየታመሰ ይገኛል። ይህንን ተከትሎ አሰልጣኙ የቡድናቸውን የተጨዋቾች አማራጭ ለማስፋት ገበያ ወጥተዋል። በቅርብ ቀንም የወልቂጤ ከተማው የመስመር ተጫዋች ሄኖክ አወቀን የግላቸው ለማድረግ መቃረባቸውን ሶከር ኢትዮጵያ አረጋግጣለች።

ከኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ የተገኘውና ለፋሲል ከነማ እና ኢኮስኮ የተጫወተው ባለተሰጥኦው ተጨዋች የተሻለ የመጫወት እድል ለማግኘት ከወልቂጤ በመልቀቅ ወደ ባህር ዳር የሚያደርገውን ጉዞ በቀጣዮቹ ቀናት እንደሚያጠናቅቅ ሲጠበቅ ለባህር ዳር ጥሩ አማራጭ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

©ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ