የከፍተኛ ሊግ 7ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ነገ እና እሁድ ይደረጋሉ

 

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ 7ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ነገ እና እሁድ በሚደረጉ ጨዋታዎች ይቀጥላል፡፡ በተቀራራቢ ደረጃ ላይ የሚገኙ ክለቦች የሚያደርጉት ፍልሚያም ይጠበቃል፡፡

የምድብ ሀ ሁሉም ጨዋታዎች እሁድ የሚደረጉ ሲሆን በ1 ነጥብ ልዩነት በደረጃ ሰንጠረዡ 2ኛ እና 3ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጡት ፋሲል ከተማ እና መቀለ ከተማ ጎንደር ላይ የሚያደርጉት ጨዋታ ከፍተኛ ግምት የሚሰጠው ነው፡፡ በባህርዳር ደርቢ ባህርዳር ከተማ ከ አማራ ውሃ ስራ ማክሰኞ ሲጫወቱ መሪው አአ ፖሊስ ሱሉልታ ከተማን እሁድ ያስተናግዳል፡፡

በርካታ የአማራ ውሃ ስራ ተጫዋቾች በኢንፍሎዌንዛ በመጠቃታቸው እሁድ ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ ወደ ማክሰኞ ተዘዋውሮላቸዋል፡፡

የምድብ ሀ 7ኛ ሳምንት ጨዋታዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡

HL A

 

የምድብ ሀ የደረጃ ሰንጠረዥ

A

በምድብ ለ ሁለት ጨዋታዎች ነገ ሲደረጉ ቀሪዎቹ ጨዋታዎች እሁድ ይካሄዳሉ፡፡ መሪው አአ ከተማ ወደ ነገሌ ሲያመራ ተከታዩ ጅማ አባ ቡና ባለፈው ሳምንት ድንቅ ውጤት ያስመዘገበው ጂንካ ከተማን ያስተናግዳል፡፡

የምድብ ለ 7ኛ ሳምንት ጨዋታዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡

HL B

የምድብ ለ የደረጃ ሰንጠረዥ

B

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *