Soccer Ethiopia

መድሀኔ ብርሀኔ ከስሑል ሽረ ተለያይቶ ወደ ሀዲያ ሆሳዕና አምርቷል

Share

ባለፈው ክረምት ስሑል ሽረን የተቀላቀለው መድሀኔ ብርሃኔ ከቡድኑ ጋር በስምምነት ተለያይቶ ወደ ሀዲያ ሆሳዕና አምርቷል።

ከደደቢት ጋር የተሳካ ዓመት ካሳለፈ በኋላ በክረምቱ ዝውውር መስኮት የመጨረሻ ቀን ስሑል ሽረን የተቀላቀለው ሁለገቡ መድሀኔ ብርሀኔ በስሑል ሽረ ቆይታው መስመር ተከላካይነት ፣ በመስመር ተጫዋችነት እና በፊት አጥቂነት መጫወት የቻለ ሲሆን በሊጉ የመጀመርያ ሳምንታት ቡድኑን በቋሚነት ቢያገለግልም ቆይቶ ባልታወቀ ምክንያት ቡድኑን ማገልገል አልቻለም።

ከደደቢት ታዳጊ ቡድን አድጎ እስከ ባለፈው ዓመት ከሰማያዊዎቹ ጋር ቆይታ የነበረውና በመሐል ለቢሾፍተለ አውቶሞቲቭ የተጫወተው ይህ ተጫዋች ባስገባው የልቀቁኝ ደብዳቤ መሰረት ከቡድኑ ጋር በስምምነት ተለያይቶ ዛሬ አራተኛ የክለቡ ፈራሚ በመሆን ሀዲያን ተቀላቅሏል።

ሀዲያ ሆሳዕና ከመድሃኔ በፊት ሳሊፍ ፎፋና፣ ተስፋዬ አለባቸው እና ቢኒያም ሲራጅን ማስፈረሙ ይታወቃል።

©ሶከር ኢትዮጵያ

ሶከር ኢትዮጵያ

ሶከር ኢትዮጵያ በ ‘አብርሀም ገ/ማርያም የማስታወቂያ ድርጅት’ ስር የሚሰራ ድረገፅ ሲሆን በኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ በሚያተኩሩ ዜናዎች፣ ቁጥራዊ መረጃዎች፣ ታሪኮች፣ ጥልቅ ዘገባዎች፣ አስተያየቶች እና ትንታኔዎች ላይ ትኩረቱን ያደርጋል።

ዘርፍ

ማኅደር

top