ከቀናት በፊት አዲስ አሰልጣኝ የቀጠሩት እና በዝውውር መስኮቱ ተሳትፎ ያደርጋሉ ተብለው ሲጠበቁ የነበሩት ስሑል ሽረዎች የተከላካይ አማካዩ አስራት መገርሳን አስፈርመዋል።
ባለፈው የውድድር ዓመት አጋማሽ ከወልዋሎ ጋር የተለያየው አማካዩ ወደ ስሑል ሽረ ማምራቱን ተከትሎ የቡድኑ ሥስተኛ ፈራሚ መሆን ችሏል።
ከዚህ ቀደም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን ጨምሮ በኢትዮ-ኤሌክትሪክ፣ ዳሽን ቢራ፣ ደደቢት፣ ወልዋሎ እና የእስራኤሉ ሀፖይል ኒል ራማት ኤል ሐሻሮን የተጫወተው ይህ አማካይ ለቋሚ ተሰላፊነት ከሀብታሙ ሽዋለም ብርቱ ፉክክር ይጠብቀዋል።
ስሑል ሽረዎች ከዚህ ቀደም ዮናታን ከበደ እና ራሂም አስማኑን አስፈርመው ከመድሃኔ ብርኃኔ ጋር ደግሞ በስምምነት መለያየታቸው ይታወሳል።
© ሶከር ኢትዮጵያ