የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሊግ ሶስተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከነገ ጀምሮ ይካሄዳሉ 

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሊግ 3ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ከቅዳሜ እስከ ማክሰኞ በሚደረጉ ጨዋታዎች ይቀጥላል፡፡ የምስራቅ ፣ የመካከለኛው ፣ የሰሜን ሀ እና የደቡብ ለ ክለቦች የ3ኛ ሳምንት ጨዋታቸውን ሲያደርጉ የደቡብ ሀ ክለቦች የ1ኛ ሳምንት ጨዋታቸውን ያከናውናሉ፡፡ በሰሜን ዞን ምድብ ለ ደግሞ ቡድኖች በዚህ ሳምንት አራፊ በመሆናቸው ጨዋታ አይደረግም፡፡

የዚህ ሳምንት መርሃ ግብር የሚከተለው ነው፡-

 

ምስራቅ ዞን (3ኛ ሳምንት)

ቅዳሜ 12/06/2008

09፡00 አሊ ሐብቴ ጋራዥ ከ መተሃራ ስኳር (ድሬዳዋ)

እሁድ 13/06/2008

09፡00 ሀረር ሲቲ ከ ካሊ ጅግጅጋ (ሐረር)

09፡00 ኢትዮ ሶማሌ ከ ቢሾፍቱ ከተማ (ጅግጅጋ)

09፡00 ወንጂ ስኳር ከ ሞጆ ከተማ (ወንጂ)

 

መካከለኛ ዞን ሀ (3ኛ ሳምንት)

እሁድ 13/06/2008

09፡00 መቂ ከተማ ከ ለገጣፎ (መቂ)

07፡00 ዱከም ከተማ ከ የካ (ድከም)

ንፋስ ስልክ ከ ልደታ (አበበ ቢቂላ ፣ ቀን እና ሰአት በፌዴሬሽኑ አልተገለጸም)

ቦሌ ከ ቱሉ ቦሎ (አበበ ቢቂላ ፣ ቀን እና ሰአት በፌዴሬሽኑ አልተገለጸም)

 

መካከለኛ ዞን ለ (3ኛ ሳምንት)

እሁድ 13/06/2008

09፡00 ወሊሶ ከተማ ከ ሆለታ ከተማ (ወሊሶ)

09፡00 ወልቂጤ ከ ቦሌ ገርጂ ዩኒየን (ወልቂጤ)

ማክሰኞ 15/06/2008

09፡00 አራዳ ከ አምቦ ከተማ (አበበ ቢቂላ)

05፡00 አዲስ ከተማ ከ ጨፌ ዶንሳ (አበበ ቢቂላ)

 

ደቡብ ዞን ሀ (1ኛ ሳምንት)

እሁድ 13/06/2008

09፡00 መቱ ከተማ ከ ጋምቤላ ከተማ (መቱ)

09፡00 ከፋ ቡና ከ አሶሳ ከተማ (ቦንጋ)

09፡00 ሚዛን አማን ከ ዩኒቲ ጋምቤላ (ሚዛን አማን)

-ይህ ዞን ከሌሎች ዘግይቶ ለመጀመር የተገደደ ሲሆን በዚህ ሳምንት የ1ኛ ሳምንት ጨዋታውን ያደርጋል፡፡

 

ደቡብ ዞን ለ (3ኛ ሳምንት)

እሁድ 13/06/2008

09፡00 ጋርዱላ ከ ሮቤ ከተማ (ጋርዱላ)

09፡00 ወላይታ ሶዶ ከ ሀንበሪቾ (ቦዲቲ)

09፡00 ኮንሶ ኒውዮርክ ከ ቡሌ ሆራ (ኮንሶ)

09፡00 ጎባ ከተማ ከ ጎፉ ባሪንቼ (ጎባ)

 

ሰሜን ዞን ሀ (3ኛ ሳምንት)

እሁድ 13/06/2008

09፡00 ደብረማርቆስ ከተማ ከ ደባርቅ ከተማ (ደብረማርቆስ)

09፡00 ዳባት ከተማ ከ ዳሞት ከተማ (ዳባት)

09፡00 አዊ እምፒልታቅ ከ አማራ ፖሊስ (እንጅባራ)

የሰሜን ዞን ምድብ ለ ቡድኖች በዚህ ሳምንት አራፊ በመሆናቸው ጨዋታዎች አይደረጉም፡፡

ያጋሩ