6 ክለቦች እየተሳተፉበት የሚገኘው የኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ደቡብ – ምስራቅ ዞን የ1ኛው ዙር እሁድ በሚደረጉ 3 ጨዋታዎች ይጠናቀቃል፡፡
በ8 ነጥብ የዞኑ አናት ላይ የሚገኘው ሲዳማ ቡና ወደ አዳማ ተጎዞ አዳማ ከተማን ይገጥማል፡፡ የአሰልጣኝ በሃይሏ ዘለቀ ቡድን እስካሁን ሽንፈት ያላጋጠመው ብቸኛው የዞኑ ቡድን ነው፡፡
በ7 ነጥቦች 2ና ደረጃ ላይ የሚገኘው ሀዋሳ ከተማ ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚን 09፡00 ላይ ሲያተናግድ ድሬዳዋ ላይ ድሬዳዋ ከተማ አርባምንጭ ከተማን ይገጥማል፡፡ በድሬዳዋ የከፍተኛ ሊግ ጨዋታ 8፡00 ላይ የሚደረግ በመሆኑ ይህ የድሬዳዋ እና አርባምንጭ ጨዋታ 10፡00 ላይ ይደረጋል፡፡
እሁድ 13/06/2008
09፡00 አዳማ ከተማ ከ ሲዳማ ቡና (አዳማ አበበ ቢቂላ)
09፡00 ሀዋሳ ከተማ ከ ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ
10፡00 ድሬዳዋ ከተማ ከ አርባምንጭ ከተማ
የዞኑ የደረጃ ሰንጠረዥ ይህንን ይመስላል፡-
ፎቶ – በዞኑ ከሚሳተፉ ክለቦች አንዱ የሆነው ድሬዳዋ ከተማ