አአ ተስፋ ሊግ ፡ ንግድ ባንክ መሪነቱን ሲያሰፋ ደደቢት ከመከላከያ አቻ ተለያዩ 

የአዲስ አበባ እግርኳስ ፌዴሬሽን የሚያዘጋጀው የአዲስ አበባ ተስፋ ሊግ የ8ኛ ሳምንት ሁለት ጨዋታዎች ዛሬ በአበበ ቢቂላ ተካሂደው መሪው ንግድ ባንክ መሪነቱን አስፍቷል፡፡ ደደቢት እና መከላከያ ደግሞ አቻ ተለያይቷል፡፡

በ3፡00 የኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚን የገጠመው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 3-1 በሆነ ውጤት አሸንፏል፡፡ ለንግድ ባንክ ሞላለት ያለው ሁለት ሲያስቆጥር ሙሴ ተክለወይኒ ቀሪዋን ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡ አለሙ ብርሃኑ የአካዳሚን ብቸኛ ግብ ከቅጣት ምት በድንቅ ሁኔታ ከመረብ አሳርፏል፡፡ ንግድ ባንክ ድሉን ተከትሎ በ20 ነጥብ ሊጉን መምራቱን ቀጥሏል፡፡

በ5፡00 ደደቢት ከመከላከያ 1-1 አቻ ተለያይተዋል፡፡ መከላከያ በአቤል ከበደ ግብ ቀዳሚ መሆን ሲችል እንዳለ ከበደ ደደቢትን አቻ ደረገች ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡ የአቻ ውጤቱ  ሁለቱን ቡድኖች ከመሪው ንግድ ባንክ እንዲርቁ አድርጓቸዋል፡፡

የ8ኛ ሳምንት ቀጣይ ጨዋታዎች ነገ የሚደረጉ ሲሆን በ3፡00 ምንም ጨዋታ ሳያሸንፍ በመጨረሻ ደረጃ ላይ የሚገኘው ሰውነት ቢሻው ከ ኢትዮጵያ ቡና ይጫወታሉ፡፡ 5፡00 ላይ ሙገር ሲሚንቶ ከአዳማ ከተማ ሲጫወቱ 7፡00 ላይ ቅዱ ጊዮርጊስ ከኢትዮጵያ መድን ይጫወታሉ፡፡

የደረጃ ሰንጠረዡ ይህንን ይመስላል፡-

tesfa

ያጋሩ