አዳማ ከተማ ከ ሀዲያ ሆሳዕና ፡ ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

አዳማ ከተማ 2-0 ሀዲያ ሆሳዕና
7′ አቢኮዬ ሻኪሩ
74′ ታፈሰ ተስፋዬ
———-*——–

ተጠናቀቀ!!!
ጨዋታው በአዳማ ከተማ 2-0 አሸናፊነት ተጠናቀቀ
፡፡
አዳማ የሊጉን መሪነት በ23 ነጥብ ነገ ጨዋታውን ከሚያደርገው ቅዱስ ጊዮርጊስ ተረክቧል፡፡

90′ መደበኛው የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ተጠናቆ 4 ደቂቃ ተጨምሯል፡፡

85′ ሚካኤል ጆርጅ ተቀይሮ ከገባ በኋላ ጥሩ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡ ሁለት ጥሩ ሙከራዎች ማድረግ የቻለ ሲሆን ታፈሰ ላስቆጠረው ግብ ማመቻቸትም ችሏል፡፡

74′ ጎልልልልል
ታፈሰ ተስፋዬ ከሚካኤል የተሻገረለትን ኳስ ተጠቅሞ የአዳማን 2ኛ ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡

72′ ሚካኤል ጆርጅ በወንድሜነህ ተቀይሮ በገባበት ቅፅበት ከእሸቱ የተሻገረለትን ኳስ በግንባሩ ገጭቶ ለጥቂት ጎል ከመሆን ድኗል፡፡
ኳሷ በረኛውን አልፎ ጎል ለመሆን እጅግ ተቃርባ የነበረ ሲሆን ቢንያም ገመቹ ከግቡ መስመር ላይ አውጥቷታል

70′ ሀብቶም ከዱላ የተሻገረለትን ኳስ ወደ ግብ መትቶ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

68′ ቡልቻ ሹራ ከግራ መስመር ተነስቶ 2 ተጫዋቾች በማለፍ የመታው ኳስ አግዳሚውን ታኮ ወደ ውጪ ወጥቷል፡፡

* የአዳማ ከተማ ከንቲባ ሃብታሙ ኃ/ሚካኤል ጨዋታውን በስታድየም ተገኝተው በመከታተል ላይ ይገኛሉ፡፡

65′ ቡልቻ ሹራ ግብ አስቆጣሪው ሻኪሩን ቀይሮ ገብቷል፡፡

62′ ወንድወሰን ሚልኪያስ ወጥቶ ደሳለኝ ደባሽ ገብቷል፡፡

54′ ዱላ ሙላቱ በታከለ አለማየሁ ላይ በሰራው ጥፋት የጨዋታው የመጀመርያ የማስጠንቀቅያ ካርድ ተመዞበታል፡፡

52′ ዱላ ሙላቱ የአዳማ ተጫዋቾችን አልፎ በግምት ከ20 ሜትር ርቀት የመታው ኳስ ለጥቂት ወደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡

51′ የሆሳዕና ተከላካዮችን ስህተት ተጠቅሞ ታፈሰ ተስፋዬ ለታከለ ያሻገረለትን ኳስ ወደ ግብ መትቶ ጃክሰን ወደ ውጪ አውጥቶበታል፡፡

48′ የተጫዋች ለውጥ – ሀዲያ ሆሳዕና
ካሳሁን ገረመው እና ቢንያም ገመቹ ወጥተው አበባየሁ ዮሃንስ እና ሀብቶም ገ/ስላሴ ገብተዋል

45′ ሁለተኛው አጋማሽ ተጀመረ

——————

*የወላይታ ድቻው አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ በስታድየሙ ከተገኙ ግለሰቦች አንዱ ነው፡፡ ድቻ በ11ኛው ሳምንት አዳማ ከተማን ያስተናግዳል፡፡

ተጠናቀቀ!!!
የመጀመርያው አጋማሽ በአዳማ ከተማ 1-0 መሪነት ተጠናቋል፡፡

45′ የጨዋታው 4ኛ ዳኛ ተጨማሪ 2 ደቂቃ አሳይተዋል፡፡

41′ ታፈሰ የሆሳዕና የጨዋታ ውጪ መስመር ጥሶ ከግብ ጠባቂው ጋር አንድ ለአንድ ቢገናኝም ሳይጠቀምበት ቀርቷል፡፡

36′ ሻኪሩ ከታከለ ተቀብሎ ከ18 ሜትር አክርሮ ወደ ግብ የላከው ኳስ የብረቱ አግዳሚ መልሶበታል፡፡
ሻኪሩ በድጋሚ ሌላ ኳስ ሞክሮ ኸደ ውጪ ወጥቶበታል፡፡

33′ ጨዋታው በአዳማ የግብ እና የእንቅስቃሴ የበላይነት እንደቀጠለ ነው፡፡ ወንድሜነህ ዘሪሁን በሁለት አጋጣሚዎች ጥሩ የግብ ሙከራዎች አድርጓል፡፡

27′ በጃኮብ ስህተት ምክንያት አበው ታምሩ ወርቃማ የግብ ማስቆጠር እድል አግኝቶ በማይታመን ሁኔታ ወደ ውጪ ሰዷታል፡፡

25′ ጨዋታው 25 ደቂቃዎች ተጉዟል፡፡ አዳማ ከተማ ጫና በመፍጠር የተሻለ እንቅስቃሴ እያደረገ ይገኛል፡፡ ሀዲያ ደግሞ በእንዳለ ደባልቄ እና ዱላ ሙላቱ አማካኝነት የግብ እድል ለመፍጠር በመጣር ላይ ይገኛል፡፡

13′ አበው ታምሩ የመታው ኳስ ለጥቂት ወደ ውጪ ወጥታለች፡፡

7′ ጎልልልል አቢኮዬ ሻኪሩ
ቤኒናዊው አጥቂ ከሱሌማን የተሻገረለትን ኳስ በግንባሩ በመግጨት አዳማን ቀዳሚ አድርጓል፡፡

1′ ጨዋታው ተጀመረ
አዳማ ከግራ ወደ ቀኝ ሲያጠቃ ሆሳዕና በተቃራኒው ያጠቃል፡፡

ሁለቱም ቡድኖች በማሟሟቅ ላይ ይገኛሉ፡፡

—-

የሀድያ ሆሳዕና አሰላለፍ

ጃክሰን ፊጣ
ውብሸት አለማየሁ – ንጋቱ ዱሬ – ቢንያም ገመቹ – አየለ ተስፋዬ – ሄኖክ አርፊጮ
ካሳሁን ገረመው – አበው ታምሩ – አምራላ ደልቻታ – ዱላ ሙላቱ
እንዳለ ደባልቄ
————-
የአዳማ ከተማ አሰላለፍ
ጃኮብ ፔንዛ
እሸቱ መና – ተስፋዬ በቀለ – ሞገስ ታደሰ – ሱሌማን መሃመድ
ፋሲካ አስፋው – ወንድወሰን ሚልኪያስ – ወንድሜነህ ዘሪሁን – ታከለ አለማየሁ
ታፈሰ ተስፋዬ – አቢኮዬ ሻኪሩ የጨዋታው 4ኛ ዳኛ ተጨማሪ 2 ደቂቃ አሳይተዋል፡፡

41

ያጋሩ