የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ የቅዳሜ ውሎ ፡ ቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት

ፌዴራል ፖሊስ 1-1 ባቱ ከተማ
87′ ቻላቸው ቤዛ

16′ ክንዴ አበጀ (ፍፁም ቅጣት ምት)

———————————–

ተጠናቀቀ!!
ጨዋታው 1-1 በሆነ አቻ ውጤት ተጠናቋል፡፡

ጎልልል
87′ ቻላቸው ቤዛ ከርቀት የፌዴራል ፖሊስን የአቻነት ግብ አስቆጥሯል፡፡

77′ ፌዴራል ፖሊስ ተጭኖ ቢጫወትም የግብ ማስቆጠር እድሎች መፍጠር አልቻለም፡፡

62ኛ ደቂቃ ላይ ደርሰናል፡፡ ጨዋታው የተቀዛቀዘ እንቅስቃሴ እየታየበት ነው፡፡

2ኛው 45 የጨዋታ ክፍለጊዜ ተጀመረ
————
———————–

ተጠናቀቀ!!!
የመጀመርያው አጋማሽ በባቱ መሪነት ተጠናቋል፡፡

45′ አራተኛ ዳኛው ተጨማሪ 2 ደቂቃ አሳይተዋል፡፡

40′ ጨዋታው ተመጣጣኝ እንቅስቃሴ እየተደረገበት ነው፡፡ ቻላቸው ቤዛ ቋሚ የመለሰበት ሙከራ ከፌዴራል ፖሊስ በኩል የሚጠቀስ ነው፡፡

16′ ጎልልልል
ክንዴ አበጀ የተሰጠውን የፍፁም ቅጣት ምት ወደ ግብነት ቀይሮ ባቱን ቀዳሚ አድርጓል፡፡

15′ የፍፁም ቅጣት ምት ለባቱ ተሰጥቷል፡፡ ነፃነት ለገሰ ለጥፋቱ የማስጠንቀቅያ ካርድ ተመዞበታል፡፡

1′ በፌዴራል ፖሊስ እና ባቱ መካከል የሚደረገው ጨዋታ ተጀምሯል፡፡

——————————-

አአ ዩኒቨርሲቲ 0-3 ደቡብ ፖሊስ
33′ ወንድሜነህ አይናለም
62′ 73′ ምስጋና ወልደዮሃንስ

——*—–

ተጠናቀቀ!!!
ጨዋታው በእንግዳው ቡድን ደቡብ ፖሊስ 3-0 አሸናፊነት ተጠናቋል፡፡

90′ አራተኛው ዳኛ ተጨማሪ 4 ደቂቃዎች ጨምረዋል፡፡

73′ ጎልልልል
ወንድሜነህ ለራሱ 2ኛውን ለቡድኑ 3ኛውን ግብ አስቆጥሯል፡፡

70′ አአ ዩኒቨርሲቲዎች በቀይ ካርድ ተጫዋች ከጎደለባቸው በኋላ ጥሩ እየተንቀሳቀሱ ነው፡፡ የግብ ሙከራዎች ማድረግም ችለዋል፡፡

62′ ጎልልል
ምስጋና ወልደ ዮሃንስ የደቡብ ፖሊስን 2ኛ ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡

50′ የአአ ዩኒቨርሲቲ አምበል ተመስገን ተስፋዬ በሰራው አደገኛ ጥፋት በቀጥታ ቀይ ካርድ ከሜዳ ተወግዷል፡፡ ተጫዋቹ ከሜዳ ለመውጣት አንገራግሯል፡፡

46′ የጨዋታው 2ኛ አጋማሽ ተጀምሯል፡፡

የሁለቱ ቡድን ተጫዋቾች ከመልበሻ ክፍል በመውጣት ላይ ይገኛሉ
—–

የመጀመርያው አጋማሽ ተጠናቋል፡፡

45′ የመጀመርያው አጋማሽ በደቡብ ፖሊስ መሪነት ሊጠናቀቅ ተቃርቧል፡፡ ደቡብ ፖሊሶች የተሻለ የኳስ ቁጥጥር እያሳዩ ነው

33′ ጎል ደቡብ ፖሊስ
ወንድሜነህ አይናለም ለቢጫ የእንግዳዎቹን ቀዳሚ ግብ ከመረብ አሳርፏል፡፡ ወንድሜነህ 3 ጨዋታ በተከታታይ ግብ ማስቆጠር ችሏል፡፡

16′ ጨዋታው ተመጣጣኝ እንቅስቃሴ እየተደረገበት ይገኛል፡፡
1′ ጨዋታው ተጀመረ

*አሁን ሁለቱም ቡድኖች አሟሙቀው ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል፡፡

*ጨዋታው እስካሁን አልተጀመረም፡፡ መጀመር ካለበት ሰአት 20 ደቂቃ ዘግይቷል፡፡

*በአሁኑ ሰአት የደቡብ ፖሊስ እና አአ ዩኒቨርሲቲ ቡድኖች እንዲሁም ጨዋታውን የሚመሩ ዳኞች እያሟሟቁ ይገኛሉ፡፡

———————————-

የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ 7ኛ ሳምንት ሁለት ጨዋታዎች ዛሬ በአበበ ቢቂላ ይደረጋሉ፡፡
አአ ዩኒቨርሲቲ እና ደቡብ ፖሊስ ጨዋታቸውን ለመጀመር እየተዘጋጁ ሲሆን ፌዴራል ፖሊስ ከ ባቱ ከተማ 10:00 ላይ ይጫወታሉ፡፡
ሶከር ኢትዮጵያም የሁለቱን ጨዋታዎች ዋና ዋና ሁነቶች በዚህ ገፅ ላይ በቀጥታ ታቀርብላችኀለች፡፡

———————————-

ያጋሩ