ተጫዋቾች ለትውልድ ከተማቸው ድጋፍ እያደረጉ ነው

የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ለሚደረገው ጥረት የሚረዳ የቁሳቁስ ድጋፍ አምስት ተጫዋቾች ለትውልድ ከተማቸው አድርገዋል።

የኮሮና ቫይረስ ወረረሽኝ ለመቆጣጠር በስፖርቱ ዘርፍ የተለያዩ ተቋማት እና ተጫዋቾች ድጋፍ ማድረጋቸው በቀጠለበት በአሁኑ ሰዓት የሲዳማ ቡናው አጥቂ አዲስ ግደይ፣ የመከለከያው አጥቂ ሐብታሙ ወልዴ፣ የጅማ አባ ጅፋሩ አማካይ ንጋቱ ገብረ ሥላሴ፣ የሀላባ ከተማው ልመነህ ታደሰ እና የጅማ አባ ጅፋሩ ተከላካይ መላኩ ወልዴ በጋራ በመሆን ለትውልድ ከተማቸው አጋሮ ድጋፍ አድርገዋል።

ለከተማው ከንቲባ የምግብ ዘይት ፣ የምግብ ዕህል እና ሌሎች ቁሳቁሳቁሶች ዛሬ ያስረከቡት እኝህ አምስት ተጫዋቾች በቀጣይ መሰል ድጋፎችን እንደሚያደርጉ ቃል በመግባት የአካባቢው ኅብረተሰብ በሽታውን ለመከላከል በሚደረግ ጥረት ውስጥ ሰዎች በሚበዙባቸው ቦታዎች ባለመሄድ፣ የእጅ መጨባበጥ በማቆም፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና ከምንም በላይ የጤና ባለሞያዎችን ምክር በማዳመጥ ተግባራዊ እንድታደርጉ በማለት መልክታቸውን አስተላልፈዋል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ