ወላይታ ድቻ የመስመር ተጫዋች አስፈርሟል

ወላይታ ድቻዎች ትናንት የዝውውር መስኮቱ ከመዘጋቱ ቀደም ብለው በረከት ወንድሙን ዝውውርን ፈፅመዋል፡፡

በ2008 በወላይታ ድቻ ከ17 ዓመት በታች የክለብ እግር ኳስን የጀመረው እና በ2010 ደግሞ ከ20 ዓመት የድቻ ቡድን ውስጥ ቆይታን ያደረገው ይህ ተጫዋች ዐምና የተስፋ ቡድን ቆይታው በመጠናቀቁ ምክንያት ወደ ከፍተኛ ሊጉ ሶዶ ከተማ አምርቶ ለአንድ ዓመት ከግማሽ ያህል ቆይታን ካደረገ በኃላ ዳግም ወደአሳዳጊ ክለቡ የሚመልሰውን ዝውውር ፈፅሟል፡፡

© ሶከር ኢትዮጵያ