አሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ የሚውል ድጋፍ አደረጉ

አዲሱ የቢጫዎቹ አሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ የሚውል የገንዘን ድጋፍ አደረጉ።

በዓለም አቀፍ ደረጃ አሳሳቢ የሆነውን ወረርሺኝ በሀገር ደረጃ ለመከላከል መንግስት እንቅስቃሴዎች መጀመሩን በይፋ ካሳወቀ በኋላ የእግርኳስ ማኅበረሰቡ እጅግ የሚደነቅ የድጋፍ እንቅስቃሴ በማድረግ ላይ ሲገኝ አሁን ደግሞ የወልዋሎው አሰልጣኝ ዘማርያም ወልደጊዮርጊስ በግላቸው የ30 ሺህ ብር ድጋፍ አድርገዋል።

ከዚህ ቀደም ቡድኖች፣ ተጫዋቾች ተሰባስበው እና በግል የተለያዩ ድጋፎች እያደረጉ መቆየታቸው ሲታወስ የበርካታ ቡድኖች ደጋፊ ማሕበራትም የሚበረታታ የማኅበረሰባዊ ድጋፎች በማድረግ ከህዝባቸው ጎን ተሰልፈዋል።

ለወረርሺኙ መከላከያ የሚሆን በርካታ የገንዘብ ድጋፍ በመለገስ የሚገኘው የእግር ኳሱ ቤተሰብ በቀጣይ ቀናትም ተጨማሪ ድጋፎች እንደሚያደርግ ይጠበቃል።

© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ