ተጫዋቾች ድጋፍ ማድረጋቸውን ቀጥለዋል

በትግራይ ክልል ክለቦች የሚገኙ ተጫዋቾች ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ እና ተያያዥ ጉዳዮች የሚያደርጉትን ድጋፍ የቀጠሉ ሲሆን ተጨማሪ ሦስት ተጫዋቾችም በጋራ ድጋፍ አድርገዋል።

ከዚህ ቀደም ሀያ የሚደርሱ በትግራይ ክለቦች የሚጫወቱ ተጫዋቾች ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ ድጋፍ ማድረጋቸው የሚታወስ ሲሆን አሁን ደግሞ ተጨማሪ ሦስት ተጫዋቾች ድጋፍ በማድረግ እንቅስቃሴውን ተቀላቅለዋል። በዚህም የስሑል ሽረው አጥቂ ሰዒድ ሐሰን እንዲሁም የደደቢቶቹ ዮሐንስ ፀጋይ እና ሐድሾም በርኸ በዛሬው ዕለት ድጋፍ ያደረጉ ተጫዋቾች ሆነዋል።

በርካታ ተጫዋቾች በግል እና በማኅበር የተለያዩ ድጋፎች ማድረጋቸው የሚታወስ ሲሆን በቀጣይ ቀናትም የተቀሩት ተጫዋቾች፣ ክለቦች እና አሰልጣኞች ድጋፍ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ