ብርቱካናማዎቹ ለኮሮና ወረርሺኝ መከላከያ የሚሆን የአንድ ወር ደሞዛቸውን ለግሰዋል።
የክለቡ ተጫዋቾችን ጨምሮ መላ አባላትን ያሳተፈው እና 1,000,061 (አንድ ሚልዮን ስልሣ አንድ ሺህ) የሚገመተውን ድጋፍ ያደረጉት ብርቱካናማዎቹ በቀጣይ ቀናትም በግንዛቤ ማስጨበጥ እና ከክለቡ ማኅበረሰብ ድጋፎችን በማሰባሰብ እንደሚቀጥሉ ለማወቅ ተችሏል።
የእግርኳስ ማኅበረሰቡ በዓለም አቀፍ ደረጃ አሳሳቢ የሆነው ወረርሺኝን ለመከላከል የገንዘብ እና የቁሳቁስ ድጋፎች ከማድረግ አልፎ በተለያዩ መገናኛ ብዙሀን ግንዛቤ በማስጨበጥም የሚመሰገን ተግባር እየፈፀመ ይገኛል።
© ሶከር ኢትዮጵያ