የጅማ አባ ጅፋር ተጫዋቾች እና ደጋፊዎች በጅማ ከተማ ለሚገኙ አቅመ ደካማ የማኅበረሰቡ አካላት ድጋፍ አድርገዋል፡፡
የቡድኑ ተጫዋቾች እና አባለት ከወር ደሞዛቸው ላይ ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ ለሚደረገው ዝግጅት የሚያግዝ 130,000 ብር ለከተማው አስተዳደር አበርክተዋል። በክለቡ ደጋፊዎች በኩል ደግሞ ለአንድ ሳምንት የቆየ የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሀ ግብር የተከናወነ ሲሆን በከተማው ለሚገኙ ከ200 በላይ ለሚሆኑ አቅመ ደካሞች ከከተማው ህብረተሰብ ያሰባሰቡትን የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁስ እና የምግብ አቅርቦት ድጋፍ አድርገዋል። ይህ በጎ ተግባር ወደፊትም የሚቀጥል እንደሆነና አቅመ ደካማዎችም በየጊዜው ክትትል እንደሚደረግላቸው ታውቋል፡፡
👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም
👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ
👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!
© ሶከር ኢትዮጵያ