የከፍተኛ ሊጉ ክለብ ቡታጅራ ከተማ ለኮሮና ቫይረስ መከላከያ እንዲውል የገንዘብ ድጋፍን አድርጓል፡፡
የኮሮና ቫይረስን የመከላከል እና ችግሩ የሚያስከትለውን ጉዳት አስቀድሞ ለመቅረፍ በሁሉም የሀገሪቱ አቅጣጫ ርብርቡ ቀጥሏል፡፡ በተለይ በሀገራችን የሚገኙ የእግር ኳስ ክለቦች፣ አሰልጣኞች፣ ተጫዋቾች እና የቡድን አመራሮች ድጋፋቸውን በቁሳቁስ እና በገንዘብ እያደረጉ ሲሆን አሁን ደግሞ ከኢትዮ-ኤሌክትሪክ በመቀጠል ሁለተኛው የከፍተኛ ሊግ ክለብ ቡታጅራ ከተማ ሆኗል፡፡ ቡድኑ ከአሰልጣኞች እና ከቡድኑ ተጫዋቾች የወር ደመወዝ በመቁረጥ ከ51 ሺህ ብር በላይ ለዚህ በጎ አላማ እንዲውል በዛሬው ዕለት አበርክቷል፡፡
👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም
👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ
👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!
© ሶከር ኢትዮጵያ