የስልጤ ወራቤ እግር ኳስ ክለብ የገንዘብ ድጋፍን አድርጓል፡፡
ለኮሮና ቫይረስ መከላከል በሚደረገው ድጋፍ ሁሉም የራሱን ድርሻን በተገኘው አጋጣሚ ሁሉ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ በተለይ በስፖርቱ ላይ የተሰማሩ አካላት በነቂስ እየተሳተፉ ሲገኝ የዚህን በጎ ተግባርም የከፍተኛ ሊጉ ተሳታፊ ስልጤ ወራቤ ተቀላቅለታል፡፡ ክለቡም ከቡድኑ የአሰልጣኝ ቡድን አባላት እና ከሁሉም ተጫዋቾች ከወር ደመወዛቸው ላይ ከሚቆረጥ በአጠቃላይ 90 ሺህ ብር ከክለቡ ደጋፊዎች ደግሞ የተሰበሰበ 25 ሺህ ብር በድምሩ አንድ አመቶ አስራ አምስት ሺህ ብር ለስልጤ ዞን አስረክቧል፡፡ ክለቡም አሁን ካደረገው ድጋፍ በተጠናከረ መልኩ በቀጣይም አጠናክሮ እንደሚቀጥል ሶከር ኢትዮጵያ ከክለቡ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል፡፡
👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም
👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ
👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!
© ሶከር ኢትዮጵያ