የጣናው ሞገድ ተጨዋቾች የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት ድጋፍ አድርገዋል

ይህንን ወረርሽኝ ለመከላከል የተለያዩ የእግርኳስ ቤተሰቦች ድጋፍ ማድረጋቸውን ሲቀጥሉ ዛሬ ረፋድ ደግሞ የባህር ዳር ከተማ ተጨዋቾች ከአሰልጣኝ ቡድን አባላት ጋር በመሆን የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል።

በክለቡ አመራሮች፣ የአሰልጣኝ ቡድን አባላት እና አምበሎች አስተባባሪነት ድጋፍ ለማድረግ ሲንቀሳቀሱ የነበሩት የቡድኑ ተጨዋቾች ዛሬ ረፋድ 460,000(አራት መቶ ስልሳ ሺ) ብር ወረርሽኙን ለመከላከል ለተቋቋመው ኮሚቴ ድጋፍ ማድረጋቸው ተሰምቷል። በቡድኑ ውስጥ ያሉት አባላት በሙሉ ከ20ሺ ብር ጀምሮ በማዋጣት ባህር ዳር በሚገኘው የዓባይ ባንክ ገቢ እንዳደረጉ ታውቋል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ

ያጋሩ