ሉሲዎቹ ኮሮና ቫይረስን ለመከላከያ የሚረዳ ድጋፍ ለማድረግ እንቅስቃሴ ጀምረዋል

የተለያዩ ግለሰቦች እና ተቋማት ይህንን ወረርሽኝ ለመከላከል የሚረዳ ድጋፍ ማድረጋቸውን ሲቀጥሉ የሉሲዎቹ ተጨዋቾች እና አሰልጣኞች የበኩላቸውን ለማድረግ እንቅስቃሴ ጀምረዋል።

በብሔራዊ ቡድኑ በዋና አሰልጣኙ ብርሃኑ ግዛው አስተባባሪነት ድጋፍ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰ እንደሆነ እና መጠኑ ለጊዜው ያልተገለፀ ገንዘብ እንደሰበሰበ ለማወቅ ተችሏል። ትላንት በጀመረው የብሔራዊ ቡድኑ ንቅናቄም ከ20 እና ከ17 ዓመት በታች የሴቶች ብሄራዊ ቡድን የአሰልጣኞች ቡድን አባላት እና ተጨዋቾች፣ የቀድሞ የሴቶች ብሄራዊ ቡድን ተጨዋቾች፣ የተለያዩ ማኅበራት እና አላማውን የሚደግፉ የተለያዩ የሉሲዎቹ ደጋፊዎች ድጋፉን እንደተቀላቀሉ ተነግሯል። እስከ ምሳ ሰዓት ድረስ ብቻ 18 ግለሰቦች በአስተባባሪዎቹ በተከፈተ የአዋሽ ባንክ አካውንት ገንዘብ ገቢ እንዳደረጉ የተገለፀ ሲሆን ከዛም በኋላ ግን በርካታ የአላማው ደጋፊዎች ድጋፍ እንዳደረጉ ተሰምቷል።

ስለ ጉዳዩ ማብራሪያ የሰጡት የብሄራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው እስከ እሁድ ድረስ ሌሎች ግለሰቦችም በተለይ የስፖርት ቤተሰቡ እንዲደግፏቸው ጥሪ አቅርበዋል።

ድጋፍ ማድረግ ለሚፈልጉ:- በአዋሽ ባንክ ቁጥር 01320103790200 – ብርሃኑ ግዛው

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ