የኢትዮጵያ እግርኳስ ተጫዋቾች ማኅበር በጎ ተግባር ሲጠቃለል

(መረጃው የስፖርት ኮሚሽን ነው)

ፕሮፌሽናል ፋትቦለርስ አሶሴሽን የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ለአቅመ ደካሞች እና ለጎዳና ተዳዳሪዎች የሚውል ያሰባሰበው ገንዘብ እና የቁሳቁስ ለሚመለከተው አካል አስረከበ።

አሶሴሽኑ ድጋፋን ያሰባሰበው ከኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ክለቦች ተጨዋቾች እና አሠልጣኞች 5,161,656.90 ብር፣ ከከፍተኛ ሊግ እግር ኳስ ክለቦች ቡድኖች 855,173 ብር እንዲሁም በኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል ፋትቦለርስ አሶሴሽን የባንክ አካውንት የተሰበሰበ 303,140 ብር በአጠቃላይ 6,319,969.90 ብር እና የተለያዩ ቁሳቁሶችን የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ለተቋቋመው ብሔራዊ ድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ አስረክበዋል።

የተሰባሰበውን ድጋፍም ክቡር አቶ ኤሊያስ ሽኩር የኢፊዲሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ፤ ክቡር አቶ ኢሳያስ ጅራ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ፕረዚዳንት እና አቶ መስፍን ብሩ የኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል ፋትቦለርስ አሶሴሽን ም/ፕረዚዳንት በጋራ በመሆን ለአምባሳደር ምስጋናው አረጋ የድጋፍ አሰባሳቢ ኮሚቴ ሰብሳቢ አስረክበዋል ።

ድጋፋም በቀጣይ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ክቡር አቶ ኤሊያስ ሽኩር እና አቶ ኢሳያስ ጅራ ጥሪያቸውን አቅርበዋል ።አምባሳደር ምስጋናው አረጋም ለተደረገፈው ድጋፍ ምስጋናቸውን ገልፀዋል።

ከአሁን በፊት የስፖርት ማህበራት ፣ ስፖርተኞች እና አሰልጣኞች በግል እና በጋራ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርጉ መቆየታቸው ይታወቃል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ