በስታዲየም ዙርያ ላሉ የጎዳና ነዋሪዎች ለአንድ ወር የሚቆይ የምገባ ስርአት ሊጀመር ነው

የተለያዩ ግለሰቦች እና ተቋማት የኮሮና ወረርሽኝ ተፅእኖን ተመቀነስ የሚረዳ ድጋፍ ማድረጋቸውን ሲቀጥሉ 300 ለሚሆኑ የጓዳና ነዋሪዎች በልተው እንዲያድሩ ለማድረግ የታሰበው ፕሮግራም ሊጀመር ነው።

በመላው የሀገሪቱ ክፍል የኮሮና ቫይረስ ለመከላከል እና አቅመ ደካሞችን ለመርዳት የሚደረገው ድጋፍ ተጠናክሮ በቀጠለበት በዚህ ጊዜ የኤፌዴሪ ስፖርት ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን እና የኢትዮጵያ አትሌትክስ ፌዴሪሽን ከቢጂአይ ኢትዮጵያ ጋር በመሆን በስታዲዮም ዙሪያ ለሚገኙ 300 የጓዳና ላይ ነዎሪዎች ምግብ የመመገብ ስርዓት ከፊታችን ቅዳሜ ጀምሮ የሚጀመር ይሆናል። በመክፈቻው ቀን የመንግስት ባለስልጣናት እንዲሁም ሌሎች እንግዶች በመታደም የዚህን መልካም ተግባር ጅማሮ የሚበስሩበት ቀን ይሆናል።

ከዚህ ቀደም የስፖርት ኮሚሽኑ ከተለያዩ አካላቶችን በማስተባበር የ3 ሚሊዮን ብር እንዲሁም እግር ኳስ ፌዴሪሽኑ ሆነ አትሌትክሱ ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን የዚህን ምግባረ ሰናይ ሀሳብን ከሌሎች አጋር ድርጅቶች ጋር በመሆን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተሰምቷል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ