” ይህ መሆኑ ደስ ብሎኛል ” ኤርሚያስ ኃይሉ (ጅማ አባ ጅፋር)

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ከመቋረጡ በፊት የመጨረሻውን ጎል ያስቆጠረው ኤርሚያስ ኃይሉ ይናገራል።

የ2012 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጅማሮውን ሲያደርግ ኤልያስ ማሞ ለድሬዳዋ ከተማ ሀዋሳ ከተማ ላይ በ15ኛው ደቂቃ ያስቆጠረው ጎል የውድድሩ የመጀመርያ ጎል ሆኖ መመዝገቡ ይታወሳል። ታዲያ ሊጉ 17ኛው ሳምንት ጨዋታዎች ተካሂደው እንዳለቁ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ውድድሩ ሲቋረጥ የጅማ አባ ጅፋሩ የመስመር አጥቂ ኤርሚያስ ኃይሉ በ90ኛው ደቂቃ ኢትዮጵያ ቡና ላይ ያስቆጠረው የመጨረሻ ሆኖ ለጊዜው ተመዝግቧል። ከሰዓታት በፊት በዛሬው ጥያቄያችን ብዘለዎቻችሁ መልስ መስጠት መሳተፋችሁ ይታወቃል።ይህን ተከትሎ ከኤርሚያስ ጋር የፈጠረበትን ስሜት አስመልክቶ አጭር ቆይታ አድርገናል።

” እውነት ለመናገር የእኔ ጎል የመጨረሻው እንደሆነ አላወኩም፣ አስቤም አልነበረም። እናንተ ጥያቄ ስትጠይቁኝ ነው በዘጠናኛው ደቂቃ ጎል ማስቆጠሬን አስታውሼ እኔ መሆኔ ትዝ ያለኝ። ይህ መሆኑ ደስ ብሎኛል። በዓለም የመጣውን ፈተና አንድ ሆነን በማለፍ ነገሮች ሲስተካከሉ ውድድሩ ይጀምራል ብዬ ተስፋ አደርጋለው። በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጀመርያ ጎሌ ኒያላ እያለው ደቡብ ፖሊስ ላይ ያስቆጠርኩት ጎል ሲሆን አሁን ደግሞ በጊዜያዊነት ኢትዮጵያ ቡና ላይ ያስቆጠርኩት ጎል የመጨረሻዬ ሆኗል። (ፈገግ እያለ) ”

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ