አቶ ኢሳይያስ ጂራ በቻይና አፍሪካ ታዳጊዎች ውድድር አምባሳደር ሆነው ተመረጡ

(ሙሉ መረጃው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ነው)

የቻይና አፍሪካ ታዳጊዎች ውድድር መስራች ሚስተር ሰኒ ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በላኩት ደብዳቤ በቻይና አፍሪካ የታዳጊዎች ውድድር በአፍሪካ ደረጃ በተዋቀረው የውድድር አዘጋጅ ኮሚቴ ውስጥ ክቡር አቶ ኢሳይያስ ጅራን ጨምሮ አራት ኢትዮጵያዊያን መመረጣቸውን አሳውቀዋል፡፡
በአፍሪካ ደረጃ ከተዋቀረው ኮሚቴ መካከል አራቱ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ እነሱም አቶ ኢሳይያስ ጅራ የቻይና አፍሪካ ታዳጊዎች ውድድር አምባሳደር፤ ኢንስትራክተር አንተነህ እሸቴ የውድድሩ ስራ አስፈጻሚ አባል እና የውድድሩ ቴክኒካል ዳይሬክተር፤ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ የኮሚቴው አባል እንዲሁም ጋዜጠኛ ንዋይ ይመር የውድድሩ የሚዲያ ኦፊሰር በመሆን መመረጣቸውን ሚስተር ሰኒ በላኩት ደብዳቤ አሳውቀውናል፡፡

ለመጀመሪያ ጊዜ ባሳለፍነው አመት በቻይና አፍሪካ ታዳጊዎች የእግር ኳስ ውድድር ላይ ከኢትዮጵያ የተሳተፈው ቡድን የውድድሩ ምርጥ ቡድን ተብሎ መመረጡ እና ጥሩ ተሳትፎ አድረጎ መመለሱ ይታወቃል፡፡

ዘንድሮ የሚካሄደው ውድድር በናይጄሪያ አስተናጋጅነት አቡጃ ላይ ሊደረግ ቀነ ቀጠሮ የተያዘለት ቢሆንም በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ምክንያት ላልተወሰነ ጊዜ መራዘሙን አዘጋጆቹ ኣሳውቀዋል፡፡

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ