የተጫዋቾች ችግር ገፍቶ እየወጣ ነው

ለወራት ደሞዝ ሳይከፈላቸው የቀሩ ተጫዋቾች በፌዴሬሽኑ መፍትሔ በማጣት ጉዳያቸውን ወደ ሠራተኛ እና ማኀበራዊ ጉዳይ በመያዝ መሔድ ጀምረዋል።

የ2012 የውድድር ዘመን ገና ከጅማሮ አስቀድሞ ውስብስብ ችግሮች አልፎ በጥሩ ሁኔታ መካሄድ ቢችልም በኮሮና ወረርሺን ምክንያት የሊግ ውድድሮች ሙሉ በሙሉ ለመሰረዝ ተገደዋል። ከዚህ በተጨማሪ ሰኔ 30 ኮንትራታቸው የሚጠናቀቅ ተጨዋቾች የኮንትራት ግዜያቸው እስከሚጠናቀቅ ድረስ ክለቦች ኮንትራታቸውን እንዲያከብሩ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ማሳወቁ ይታወቃል። ሆኖም ይህ ውሳኔ ቢተላለፍም በኮሮና ቫይርስ ምክንያት በጀት የለንም በማለት ከዚህ ቀድም ያልተከፈላቸው የአራት እና የሦስት ወር ደሞዛቸውን ጨምሮ ቀሪ ደሞዛቸውን ለማስቀረት ክለቦች መንቀሳቀስ መጀመራጀው ያሰጋቸው ተጫዋቾች በፌዴሬሽኑ ተስፋ በመቁረጥ ወደ ሠራተኛ እና ማኀበራዊ ጉዳይ ጥያቄያቸውን እያቀረቡ ይገኛል።

ለጊዜው የጅማ አባ ጅፋር ተጫዋቾች ደብዳቤ በመያዝ ጥያቄያቸውን አቅርበዋል። በመቀጠል ሌሎች አምስት ክለቦች ተጫዋቾች የዚህ ችግር ሰለባ በመሆናቸው በቀጣይ መሰል ደብዳቤ ያስገባሉ ተብሎ ይጠበቃል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ