አፍሪካ | በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ሁለተኛ ተጫዋች ተገኝቷል

የኦርላንዶ ፓይሬትሱ አማካይ ቤን ሞትሽዋሪ በኮሮና ቫይረስ መያዙ ክለቡ ይፋ አደርጓል።

ከሳምንት በፊት የቤን ጎርዳን ተጫዋች ኦማር ዘክሪ በቫይረሱ የተያዘ ሲሆን አሁን ደግሞ የኦርላንዶ ፓይሬትሱ አማካይ ቤን ሞትሽዋሪ በተደተገለት ምርመራ ቫይረሱ ተገኝቶበታል። ከቀናት በፊት የቫይረሱ ምልክቶች የታዩበት ይህ ደቡብ አፍሪካዊ ተጫዋች ለቀጣይ አስራ አምስት ቀናት በቤቱ ተቆጥቦ እንደሚቆይ ክለቡ ሲያስታውቅ ወቅታዊ የጤንነት ሁኔታውም በጥሩ ደረጃ እንደሚገኝ ተገልጿል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ