ፋሲል ከነማ ለካፍ ቅሬታ እንደሚያቀርብ አስታወቀ

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የዘንንሮ የውድድር ዘመን መሰረዙንና ይህን ተከትሎም በአፍሪካ መድረክ ኢትዮጵያን የሚወክል የለም በመባሉ ፋሲል ከነማ የይገባኛል አቤቱታ ለካፍ አቀርባለሁ ብሏል፡፡

የ2012 የውድድር ዘመን በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት በቅርቡ በተደረገ ውይይት ፕሪምየር ሊጉን ጨምሮ ሁሉም ውድድር መሰረዙ ይታወሳል፡፡ በውሳኔው እንደተገለፀው ኢትዮጵያን በቀጣዩ ዓመት በካፍ ቻምፒዮስ ሊግ እና ኮንፌድሬሽን ዋንጫ ላይ አትወከልም በመባሉ ሊጉን በ17 ሳምንታት የጨዋታ መርሀ ግብር በ30 ነጥቦች መቐለን በአንድ ነጥብ በልጦ በደረጃ ሰንጠረዡ አናት ላይ የተቀመጠው ፋሲል ከነማ በቻምፒየንስ ሊጉ መሳተፍ አለብኝ አልያም ጉዳዩን ወደ ካፍ እወስደዋለሁ ሲል በይፋዊ የፌስቡክ ገፅ ላይ አስፍሯል፡፡ ሶከር ኢትዮጵያም ባገኘችው መረጃ ክለቡ የሊግ ኩባንያው ምላሽ እንዲሰጠው ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን ይህ ካልሆነ ለአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሸን ቅሬታዬን አሰማለሁ ብሏል፡፡

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ