አርባምንጭ ከተማ ፌዴሬሽኑ የወሰነው ውሳኔ ተገቢ አይደለም በማለት ተቃውሞውን ገለፀ

የዘንድሮ ውድድር በኮሮና ምክንያት እንዲሰረዝ ፌዴሬሽኑ ውሳኔ ያሳለፈበት መንገድ ተገቢ አይደለም በማለት አርባምንጭ ከተማ ተቃውሞውን አሰምቷል።

በከፍተኛ ሊግ በምድብ ሐ እየመራ የሚገኘው አርባምንጭ ከተማ ለፌዴሬሽኑ በላከው ባለ ሦስት ገፅ ደብዳቤ ውሳኔው የሀገራችንን እግርኳስ ቀጣይ ዕጣ ፈንታ ያላገናዘበ፣ ከአድሏዊ አሰራር ያልፀዳ፣ ባለ ጉዳዮቹን አሳታፊ ያላደረገ፣ ፌዴሬሽኑ ያስቀመጠውን የአሰራር (ደንብ) የጣሰ እና ወጪን ጊዜን የተጫዋቾችን ቀጣይ ዕጣ ፈንታ ከግምት ያላስገባ፣ በደጋፊዎች ሥነ ልቦና ላይ የሚያሳድረውን ተፅዕኖ ያላገናዘበ አግባብ ያልሆነ ውሳኔ ነው ሲል አስቀምጧል። አያይዞም ውሳኔውን በድጋሚ እንዲያጤነው በደብዳቤው አሳስቧል።



👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ