የበርካታ ክለብ ተጫዋቾች በደሞዝ ምክንያት ችግር ውስጥ እንዳሉ ሶከር ኢትዮጵያ ከተለያዩ ክለብ ተጫዋቾች ቅሬታ ለመረዳት ችላለች።
በጉዳዩ ዙርያ ሀሳባቸው የሰጡት አብዛኞቹ ተጫዋቾቹ ክለባቸው በደሞዝ ዙርያ ሊያነጋግራቸው ፍቃደኛ እንዳልሆነ እና ሁኔታው በዚ ከቀጠለ በችግር ውስጥ እንደሚወድቁ አስረድተዋል። ከቀናት በፊት የፕሮፌሽናል ተጫዋቾች ማሕበር ስድስት ክለቦች ደሞዝ መክፈላቸውን ጠቅሶ ክለቦቹን ማመስገኑ የሚታወስ ሲሆን ደሞዝ ባልከፈሉ ክለቦች ያለውን አቋም እና የማሕበሩ አባላት የሆኑ ተጫዋቾች ቀጣይ ዕጣ ፋንታ ያለው ነገር የለም።
የክለብ አመራሮች ቀርበው እንድያናግሯቸው እና በቅርቡ መፍትሔ እንደሚሹ የተናገሩት ተጫዋቾቹ በተለይም ጀማሪ እና ታዳጊ ተጫዋቾች ችግር ውስጥ እንዳሉ ገልፀዋል።
👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም
👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ
👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!
© ሶከር ኢትዮጵያ