ባህር ዳር ከተማዎች በሊጉ ላይ ስለተወሰነው ውሳኔ ቅሬታቸውን አሰሙ

ባህር ዳር ከተማዎች የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ እንዲሰረዝ መደረጉን እንደሚቃወሙ ዛሬ በላኩት ደብዳቤ አስታውቀዋል።

ከቀናት በፊት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የሼር ካምፓኒ ከኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጋር በመነጋገር የ2012 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሙሉ ለሙሉ እንዲሰረዝ መወሰኑ ይታወሳል። ይህንን ተከትሎም በቀጣይ ዓመት ሃገሪቱን በአህጉራዊ ውድድሮች የሚወክል ክለብ እንዳይኖር መደረጉ ይታወቃል። ከዚህ ውሳኔ መነሻነት የፕሪምየር ሊጉ ብሎም የከፍተኛ ሊጉ ክለቦች በተወሰው ውሳኔ ላይ ያላቸውን ተቃውሞ እየገለፁ ይገኛሉ። ባህር ዳር ከተማም ዛሬ ለሊጉ አክሲዮን ማህበር ይህንን ደብዳቤ ልኳል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ