በኮረና ወረርሺኝ ምክንያት ባጋጠመው የፋይናስ ቀውስ ለተጫዋቾች የደሞዝ ክፍያን በምን መልኩ መፈፀም አለብን በሚል ኢትዮጵያ ቡና ከተጫዋቾቹ ጋር ውይይት አድርገው ውሳኔ አሳልፈዋል።
ለቡ በሚገኘው የክለቡ ካምፕ በተካሄደው በዚህ ውይይት አብዛኛዎቹ በክልል ከተማ የሚገኙ ሁለት ተጫዋቾች በውይይቱ ላይ አልተገኙም። ሆኖም በአዲስ አበባ የሚገኙ ተጫዋቾች ለምሳሌ አማኑኤል ዮሐንስ፣ አቡበከር ናስር፣ ሚኪያስ መኮንን፣ አህመድ ረሺድ፣ ኢያሱ ታምሩ፣ አስራት ቱንጆ ፣ ተክለማርያም ሻንቆ እና ምክትል አሰልጣኞቹ በውይይቱ ላይ ተገኝተዋል።
ለሁለት ሰዓት በቆየው ውይይታቸው በዋናነት የክለቡ ከፍተኛ ወጪ በሆነው ከተጫዋቾች የደሞዝ ክፍያ በመሆኑ እና ካጋጠመው የፋይናስ እጥረት አኳያ እናተም ሳትጎዱ ክለቡም ሳይጎዳ ተጋግዘን ይህንን ችግር እንዴት በጋራ እንለፈው የሚል ነበር። በክለቡ በኩል አማራጭ የሚለውን ሀሳብ ካቀረበ በኃላ ተጫዋቾችም ክለቡ ያለበትን ሁኔታ በመረዳት በፍቃዳቸው ተስማምተው ከቀሪው የሁለት ወር ደሞዛቸው የአንድ ወር አሞዛቸውን ሙሉ ለሙሉ እንዲቀር ወስነዋል። እንዲሁም እስከ ሰኔ ወር በሚቀረው ደሞዛቸው ላይ ከሚከፈላቸው ደሞዝ ላይ 40% ቀንሰዋል። ያልተከፈለው የአንድ ወር ደሞዛቸውን ክለቡ ነገ ገቢ እንደሚያደርግላቸውም ሰምተናል።
👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም
👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ
👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!
© ሶከር ኢትዮጵያ