የከፍተኛ ሊግ ክለቦች በጎ ተግባር ቀጥሏል

በከፍተኛ ሊግ እየተሳተፉ የሚገኘው የአዲስ አበባ ከተማ እግርኳስ ክለብ አባላት በሙሉ ለመቅዶንያ አረጋውያን እና ህሙማን መርጃ የቁሳቁስ ድጋፍ ሲያደርጉ የቤንች ማጂ ቡና ክለብ አባላትም የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ አከናውነዋል።

የአአ ከተማ ክለብ በኮሮና ወረርሽኝ ምክንያት ለተፈጠረው ማኀበራዊ ችግር ለመቅረፍ በማሰብ የወንድ፣ የሴት እና የታዳጊ ተጫዋቾችና የቡድን አባላት በጋራ በመሆን 130 ሺህ ብር የሚገመት ገንዘብ ከደሞዛቸው በማዋጣት ለመቅዶንያ የአረጋውያን ህሙማን መርጃ የምግብ ቁሳቀሱስ፣ የንፅህና መጠበቂያ እና የአልባሳት ድጋፍ አድርገዋል።

ይህን በጎ ተግባር በማስተባበር የክለቡ ሥራ አስኪያጅ አቶ ነፃነት ትልቁን አስተዋፆኦ ያደረጉ ሲሆን በተጓዳኝ ክለቡ የሚጠቀምበትን የመመላለሻ አውቶብስ ለከተማዋ ነዋሪ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲሰጥ መወሰኑን ሰምተናል። ከዚህ ቀደም ለመቅዶንያ የ100 ሺህ ብር የገንዘብ ድጋፍ እንዳደረገ የሚታወቀው የአደከስ አበባ ከተማ እግርኳስ ክለብ በቀጣይም መሰል ድጋፎችን ማድረጉን እንደሚቀጥል ለማወቅ ችለናል።

ከከፍተኛ ሊግ ክለቦች ጋር በተያያዘ ከዚህ ቀደም የቤንች ማጂ ቡና ክለብ “እኛም ይመለከተናል” በሚል ርዕስ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ከደጋፊ ማህበሩ ጋር በመሆን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን አከናወኗል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ