መፍትሔ ያስገኛል የተባለለት የመንግስት የገንዘብ ድጋፍ ከምን ደረሰ ?

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ሁሉም ውድድሮች መሰረዛቸው ተከትሎ ክለቦች ካለባቸው የፋይናስ ቀውስ እንዲያገግሙ በማሰብ ፌዴሬሽኑ ለመንግስት አካለት የጠየቀው የገንዘብ ድጋፍ ከምን ደረሰ ?

ለወትሮም ደካማ የፋይናንስ መሰረት ላይ የቆሙት ክለቦች በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ውድድሮች መሠረዛቸው ለበለጠ የፋይናስ ቀውስ እንዲዳረጉ አድርጓቸዋል። ለተጫዋቾች የወራት ደሞዝ ለመክፈልም ሆነ እንደ ክለብ የመቀጠል አደጋ ውስጥ የሚገኙት ክለቦች ካጋጠማቸው ችግር እንዲያገግሙ በማሰብ የእግርኳሱ የበላይ አካል ፌዴሬሽኑ በስሩ ለሚገኙት ለፕሪምየር ሊግ ሴት እና ወንዶች፣ ከፍተኛ ሊግ ፣ ለአንደኛ ሊግ ክለቦች የገንዘብ ድጎማ ሊያደርግላቸው ይገባል በማለት ለኢፊዲሪ ስፖርት ኮሚሽን ከሰነድ ጋር የተያያዘ ደብዳቤ ባለፉት ሳምንታት መጠየቁ ይታወሳል። በጎ ምላሽ እንደሚገኝበት ተስፋ የተጣለበት ይህ ጉዳይ እስካሁን መልስ ሳያገኝ መዘግየቱ ክለቦችን የበለጠ አሳስቧል።

ለጉዳዩ ቅርበት ካላቸው ምንጮቻችን ባገኘነው መረጃ ከ40 ሚሊዮን ብር በላይ የመንግስት ድጎማ ይገኝበታል የተባለለትን ይህን ጉዳይ የፌዴሬሽኑ ፕሬዝደንት አቶ ኢሳይያስ ጅራ በሚገባ እየተከታተሉት እንደሆነ የሰማን ሲሆን በቅርቡም የገንዘብ ሚንስቴርም የገንዘቡን ድጋፉን ገቢ እንደሚያደርግ ለክለቦች ለማወቅ ችለናል።

በሌላ ዜና በቅርቡ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ከእግርኳሱ የበላይ አካል ፊፋ የገንዘብ ድጎማ እንዳደረገ ቢገለፅም ፊፋ እስካሁን ለአባል ሀገራቱ ገንዘቡን አከፋፍሎ እንዳልሰጠ ሰምተናል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ