ሶከር ታክቲክ | ከኋላ መስርቶ የመጫወት ሥልጠና

አሰልጣኝ ደስታ ታደሰ ከተለያዩ ድረ-ገጾች ያገኛቸውን የእግርኳስ ታክቲክ ንድፈ-ሐሳቦችን የተመለከቱ ጥልቅ ትንተናዎች፣ የሥልጠና መመሪያዎች እና መጻህፍትን ከእንግሊዘኛ ወደ አማርኛ በመተርጎም ሌሎች አሰልጣኞችና አንባቢን ይጠቅም ዘንድ ጥቅም ላይ ለማዋል ይሞክራል፡፡ ከዚህ በታች የቀረበው ፅሁፍም አንዱ አካል ነው፡፡


መግቢያ

በዘመናዊ እግር ኳስ በጣም እየተዘወተሩ ከሚገኙ ሒደቶች መካካል አንዱና ዋነኛው የነቃ ኳስ ቁጥጥር ላይ ወዳተኮረ ጨዋታ መሸጋገር ነው፡፡ ይህ የጨዋታ ዘይቤ በጣም የተዋወቀው ከ2009-11 በነበረው የጓርዲዮላው ባርሴሎና ቡድን ውስጥ ነው። ከዚያም በውጤታማው የስፔን ቡድን እና በጀርመኑ ባየርን ሙኒክ ክለብ ቀጥሏል፡፡ይህ አዝማምያ በተለይም በታዳጊዎች ስልጠና በደንብ ይታያል፡፡

በዚህም የብዙ አገራት ፌዴሬሽኖች ቴክኒካዊ ክህሎት ያላቸውና ኳስን በቁጥጥር ሥር በማድረግ ውጤት ማምጣት የሚችሉ ተጫዋቾችን ለማፍራት ይህንን የጫወታ ዘዴ እና አሰላለፍ በመከተል ላይ ይገኛሉ፡፡

ኳስን የመቆጣጠር ቁልፍ ክፍል ከኋላ መስርቶ የመጫወት ብቃት ነው ፡፡ይህ በአጭሩ ከግብ ጠባቂው መጀመር ማለት ነው ፡፡የጋርዲዮላ ባርሴሎና የዚህ አጨዋወት ምርጡ ምሳሌ ነው፡፡ምንም እንኳን የባርሴሎና ዘይቤን ለመከተል የሚሞክሩ ቡድኖች የእነርሱን ያህል ጥራት ባይኖራቸውም ታዳጊዎችን ከኋላ ኳስን መስርቶ ማጫወት ለታዳጊዎቹ ተጫዋቾች ጥቅም አለው ፡-

1. የኳስ መንካት ቁጥራቸውን ይጨምራል፡፡ይህም የቴክኒክ ክህሎታቸውን ይጨምራል

2. ተጫዋቾች በኳስ ቁጥጥር አላማ እንዲኖራቸው ያስተምራል

3. ለታዳጊዎች ሲጫወቱት በጣም አዝናኝ ይሆንላቸዋል ፡፡

የመጀመሪያው የኳስ ቅብብል ጥርት ያለ ከሆነ ሌላው ነገር ሁሉ ቀላል ነው ፡፡ነገር ግንአንድን ቡድንስለ ኳስ ምስረታ ማሰልጠን ተጫዋቾችን እንደማዘዝ ቀላል ተግባር አይደለም ፡፡የጋርዲዮላን ባርሴሎና እንደ ጉዳይ ጥናት (case study) ስንመለከት ከኋላ ንፁህ የኳስ ቅብብል እድገት እንዲኖር ግልፅና የተወሰነ መዋቀር አለው ፡፡ይህ መዋቀር የሚያስፈልገው ተጫዋቾች በሚናቸው ግልፅ መረዳት እንዲኖራቸውና ውጤታማ የኳስ ቁጥጥር መርህ መፈፀሙን ለማረጋገጥ ነው፡፡ይህም ተቃራኒ ቡድንን በስፋትና በጥልቀት (በአቋቋም ) መለጠጥ ኳስን በጥሩ ፍጥነት ማሰራጨት እና የቡድን አጋሮች ተቃራኒ ቡድን ለማጥቃት በጥሩ ጊዜ አጠባበቅና ወደፊት ዞረው ሊቀበሉ የሚችሉበት የተሻለ ቦታ ላይ ሲሆኑ ወደፊት መጫወት ያስችለቸዋል፡፡

(በንፅፅር ቀጥተኛ የኳስ ምስረታን እንደጨዋታ ዘይቤያቸው የሚከተሉ ቡድኖች ኳስን በጥልቀት ወደፊት የተክለሰውነት የበላይነት ላለው ተጫዋች የማሰራጨት መርህ በመያዝ በቀጥተኛ ጥልቀት በመቆም እና ወደ ፊት ያለ ተጫዋች ለመጀመሪያ ኳስ እንዲታገል በማድረግ አጋዥ ተጫዋች ሁለተኛውን ኳስ ይጠብቀል)

ጉዳይ ጥናት፡-የጓርዲዮላ ባርሴሎና (2009-11)

ወደ ባርሴሎና ጥናት ስንመለስ ጋርዲዮላ በላማሲያ ያደጉ ሁሉም ተጫዋቾች የሰለጠኑበትን ባህላዊውን 4-3-3 አሰላለፍ ይጠቀማል ፡፡ኳስ ከግብ ጠባቂው ሲጀመር የተጫዋቾች የመጀመሪያ አቋቋም ይህንን ይመስላል፡፡

ከዚህ የመጀመሪያ አቋቋም ነው ባርሴሎናዎች ማጥቃታቸውን የሚጀምሩት ፡፡ኳስን በቁጥር ብዙ ወደሆኑበት ቦታ በመውሰድ ወይም ቀድም ብሎ እንደተጠቀሰው የቡድን አጋር ከተቃራኒ ቡድን ነፃ ሆኖ ወደ ፊት ዞሮ መቀበል በሚያስችል የተቃራኒ ቡድን የመከላከል ቅርፅ መረበሽ፡፡

የግብ ጠባቂው አብዛኛው የኳስ ማቀበል ሒደት የጎንዮሽስፋት ለመፍጠር ወደ ፍፁም ቀጣት ምት ክልል መስመር ዳር ለሚያሰፉት የመሀል ተከላካቹ ይሆናል፡፡

ኳስ የሚቀበለው ተከላካይ የተቃራኒ ቡድንን ፕረሲንግ ወደ አንደኛው የሜዳ ክፍል ያደርገዋል ፡፡ይህም በተቃራኒ ያለው የሜዳ ክፍል ላይ ክፍተት እንዲፈጠር ያደርጋል፡፡

ለምሳሌ፡-በብቻ 9 ቁጥር ብቻ ለሚጫወት የሁለቱ ተከላካዮች መለጠት የኳስ ስርጭቱ ፈጣን ከሆነ 9 ቁጥሩ ሁለቱንም ተከላካዮች ፕረስ ማድረግም መያዘም አይችሉም፡፡

የግብ ጠባቂው የመጀመሪያ ኳስ ማቀበል ለአንደኛው የመሀል ተከላካይ በፍፁም ቅጣት ምት ክልል ጫፍ ላይ ይሆናል ፡፡ይህ ማለት ብቸኛው 9 ቁጥር አንዱን ጎን ብቻ ነው ፕረስ ማድረግ የሚችለው ፡፡ይህም ኳስ የያዘው ቡድን ወደፊት ለመሄድ በሌላኛው አቅጣጫ ክፍተት እንዲያገኝ ያስችለዋል ፡፡

በባርሴሎና የኳስ ቁጥጥሩን ለመጨመር የመስመር ተከላካዮች ወደፊት ተጠግተውና አስፍተው መቆማቸው በጣም አስፈላጊ ነው፡፡

አንድ ቡድን የኳስ ምስረታውን የሜዳውን ሙሉ ስፋት በመጠቀም ካደረገ ተቃራኒ ቡድን መጠጋጋቱን ጠብቆ ሁሉንም ቦታዎች በበቂ ሁኔታ መሸፈን ከአቅም በላይ ይሆንበታል ፡፡

ጆናታን ዊልሰን በተገቢው መንገድ እንዳስቀመጠው

“ጠቅላላ የሜዳው ስፋት (100-130 ሜ.በ 50-100 ሜ በልምምድ 110ሜ.በ 68 ሜ ነው፡፡በዚህም 10 ሜዳ ላይ ያሉ ተጫዋቾች ለመሸፈን በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡ብርድልብሱን በፈለከው መንገድ ሳበው ሁልጊዜም የሆነ ቦታ ክፍት ይሆናል፡፡”

ስለዚህም ከኋላ 4 ተጫዋቾች ስፋቱን በአግባቡ በመጠቀም ኳስ ስርጭቱን በተገቢው ፍጥነትና ጊዜ በማድረግ ባርሴሎና ወደ ፊት ለመጫወት ምርጡን አፍታ ለመፍጠር ተቃራኒ ቡድንን በሜዳው ሙሉ ያንቀሳቅሷቸዋል፡፡

ተቃራኒ ቡድንን በቁመት ለመለጠጥ ጥልቀትም በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ከዚህ የተነሳ የማጥቃትተጫዋቾች ቦታ አያያዝ ከፍ ያለ ሆኖ የመስመር ና አጥቂዎቹ ቀጥተኛ ጫና በማድረግ ወደ ኋላ እንዲገፏቸው በማዘዝ ኳስ ለያዙት ተጫዋቾች በጥልቅ ቦታ ላይ ክፍተት መፍጠር ፡፡

ጋርዲዮላ እንዳለው

“ የቡድን አጋርህን ለመርዳት ከእርሱ ራቅ እንጂ ወደ እርሱ አትጠጋ”

ምናልባት በጣም አስፈላጊው ክፍል የመሀል ክፍሉ ይሆናል፡፡የጋርዲዮላ ተመራጭ የመሀል ክፍል ቅርፅ በመሀል የተገለበጠ ምስል ያለው በመሆኑ አማካዮቹ (1-2) በመሆን ይቆማሉ ስለዚህ ሰርጂዮ ቡስኬትስ እንደ ብቸኛ 6 ቁጥር ይጫወታል፡፡ቡስኬትስ አስደናቂ የአጨዋወት ብልሃት አለው፡፡ባርሴሎና ከኳስ ጋር ወደፊት እንዲጠጋ አማካዩ ቦታ ደጋግሞ ይቀያይራል፡፡እንደ ጠቅላላ ህግ መነሻ ቦታው በሁለቱ የመሀል ተከላካዮች እና በመስመር ተከላካዮቹ ቀጥታ መስመር ላይ ነው፡፡

ሰርጂዮ ቡስኬትስ መነሻ ቦታው እዚህ ላይ ተቀምጧል ፡፡የተለመዱ እንቅስቃሴዎቹ በቀስቱ ተጠቁመዋል፡፡

ነገር ግን በድጋሜ ተቃራኒ ቡድንን ለማንቀሳቀስና የቁጥር ብልጫ ለመፍጠር የቡስኬት በኳስ ቁጥጥር ጊዜ ያለው ሚና እንደተቃራኒ ቡድን ቅርፅ ይወሰናል፡፡

ለምሳሌ፡-በመጀመሪያ መስመሩ በ 2 ተጫዋች ከሚከላከል ቡድን ጋር (4-4-2 ወይም 3-5-2) ቡስኬት ወደ መሀል ተከላካዮቹ መሀል በመግባት ኋላ ላይ 3 ለ2 ሁኔታን ይፈጥራል ፡፡ይህ በተዘዋዋሪ የመስመር ተከላካዮች ወደ ፊት በመጠጋት ለመሃል ተከላካዮች እና ለመሃል ተጫዋቾች ክፍተትን ይፈጥራሉ፡፡

በሁለቱ የመሃል ተከላካች መሃል ለመግባት ቀጥተኛ እንቅስቃሴ ቡስኬትስ በቡድኑ የኳስ ምስረታ ላይ የ3 ለ2 ሁኔታን ይፈጥራል

ሁለቱ ተጠግተው ያሉ የመሀል ተጫዋቾች በኳስ ምስረታው ላይ የተለያዩ ስራዎች አላቸው ፡፡በ “ከፍተኛ/ዝቅተኛ” መርህ በመቆም አንዱ በሜዳው የላይኛው ክፍል ሲጠጋ ሌላኛው ደግሞ ወደ ኋላ መለስ ይላል፡፡በአብዛኛው ዣቪ ወደ ኋላ መለስ በማለት በቀኝ ግማሽ ክፍተት(half space) ከቡስኬት ጋር በተመሳሳይ መስመር ይሆናል፡፡

የምናሰለጥነው እንዴት ነው?

ተጫዋቾችን የኳስ ምስረታ ለማስተማር ተግባራዊ አቀራረብ የሚሆነው ጨዋታ የሚመስል የታክቲክ ልምምድ ማዘጋጀት ነው፡፡ከዚያም የሚፈለገወ ኳስ ምስረታ ላይ ትኩረት መስጠት፡፡የተቃራኒ ቡድን ጫና ያለባቸው ልምምዶችና 7 ለ7 እና 8 ለ8 የመሳሰሉት የልምምድ ጨዋታዎች ለተጫዋቾች ጨዋታን የሚመስሉ ብዙ ሁኔታዎችን በመፍጠር ጨዋታዎች ላይ መረዳት ፣ውሳኔ አሰጣጥና የጨዋታ ምስረታ አተገባበርን ያሻሽላሉ፡፡

የጨዋታ ምስረታ በማሰተማር የምንፈልገውን ግብ ለማሳካት ልምምድ ለመፍጠር የተወሰኑ ህጎችንና ገደቦችን መተግበር ይቻላል፡፡ለምሳሌ ኳስ የነጠቀው ቡድን ሁልጊዜ ከግብ ጠባቂው እንዲጀምር ማድረግ እና የተፈለገውን ግብ ለማሳካት ውጤታማ ኳስ ምሰረታ ያደረገውን ቡድን ማበረታታት፡፡

ለኳስ ምሰረታ የታክቲካዊ ልምምድ ምሳሌ ፡፡ሰማያዊ የለበሰው ቡድን ሁልጊዜ ከግብ ጠባቂው በመጀመር ከሦስት በአንዱ ጎል ለማስቆጠር መሞከር ፡፡ቀዩ ቡድን ኳስን በ 10 ሰከንድ ውስጥ በመንጠቅ በመልሶ ማጥቃት በትልቁ ጎል ማግባት ኳስን መንጠቅ ካልቻሉ ሰማያዊው ቡድን ከግብ ጠባቂው ይጀምራል ፡፡

በዚህ ልምምድ የአሰልጣኙ ጣልቃ ገብነት ለቡድኑ እና ለተጫዋቾቹ ቁልፍ ስራ መስጠት ላይ ያተኩራል፡፡ምሳሌ ፡-የቡድን ስራ እነዚህ ላይ ያተኩራል

– በስፋትና በጥልቀት መቆም

– የተቃራኒ ቡድንን መከላካል መዋቅር ለማንቀሳቀስ ኳስን በከፍተኛ ፍጥነት ማሰራጨት

– ከፊት በጥሩ ጊዜ አጠባበቅና ክፍተት ላይ ላሉ ተጫዋቾች ወደፊት መጫወት

በ4-3-3 ለተጫዋቾች የምንሰጠው ስራ

 ግብ ጠባቂ፡-ኳስን በአጭር ነፃ ለሆነ ተጫዋች መስጠት ከዚያ ወደ ኳስ አካባቢ በመጠጋት ማገዝ

 የመሀል ተከላካዮች ፡-ወደ ፍጹም ቅጣት ምት ክልል ዳር ማስፋት ፡፡የተቃራኒን የመጀመሪያ የፕረሲንግ መስመር ለማዞር ኳስን ወደ አንድ ጎን በመቻወት በፍጥነት ደግሞ መመለስ

 የመስመር ተከላካዮች ፡-ወደፊት በመጠጋት በስፋት መቆም ከተቃራኒ ቡድን የመጀመሪያ ፕረሲንግ ውጪ መቆም ፣በራቀው እግር ኳስን በመቀበል ከተቃራኒ ቡድን በማሳለፍ በቀጣዩ የሜዳ ክፍል ጫናን መጨመር

 #6 በሁለቱ የመሀል ተከላካዮች መሀል እና በሁለቱ የመስመር ተከላካዮች በአግድምሽ መስመር መቆም ፡፡ከተቃራኒ ቡድን የመጀመሪያ ጫና ፊትን ወደፊት አዙሮ ለመቀበል መሞከር ፡፡የተቃራኒ ቡድን ጫና ከጨመረ የመጀመሪው ኳስ የመቀበያ መስመር ላይ የቁጥር ብልጫ መፍጠር ( ከመሀል ተከላካዮቹ መሀል)

 # 8 እና 10 በአግድሞሽ በተለያየ መስመር በመጫወት በተቃራኒ ቡድን መስመሮች መካከል በግማሽ ክፍተት መግባት

 ተቃራኒ ቡድን በመሀል ክፍል ሰው በሰው የመያዝ መንገድ ከተጠቀመ ፤6 ቁጥር ያየዘውን ተጫዋች ከኳስ እንዲርቅ ያደርገዋል ፡፡ይህም ለመሀል ተከላካዮቹ ኳስን ወደፊት ይዘው የሚጠጉበት ክፍተት በመፍጠር በመሀል ሜዳ የቁጥር ብልጫ እንዲኖር ያስችላል፡፡

 ተቃራኒ ቡድን በመጀመሪያ የመከላከል መስመሩ ሦስት ተጫዋቾች ከተጠቀመና በርቀት ያለውን የመስመር ተጫዋች እንዱን የመሀል ተከላካይ ከያዘው ፤ግብ ጠባቂው ኳስን ለመስመር ተከላካዩ ሊሰጥ ይችላል፡፡

ሌሎች ብዙ አማራጮች ይኖራሉ፡፡

በታዳጊዎች ስልጠና ተጫዋቾችን በኳስ ምስረታ መርሆች ላይ ቁልፍ መርሆችን ማስተማር ላይ ትኩረት መስጠት ገንቢ ሊሆን ይችላል (ምሳሌ፡ኳስ ስርጭትና ቦታ አያያዝ) በተጫማሪም በታዳጊዎች ስልጠና ወደ መጨረሻው ደረጃ ሲደርሱ እና ትልልቆቹ ተጫዋቾች የተቃራኒ ቡድን መከላከልን እንዴት መቆጣጥር እንደሚችሉከፍትኛ ትኩረት መስጠት

የመከላካል ሽግግር

ከኋላ መስርቶ መጫወትን ስናሰለጥን ትኩረት መሰጠት ያለበት ነገር ግን ብዙ የማናየው ነገር ቡድኑ ኳስ ሲያጣ የመከላካል ሽግግር እንዴት ነው የሚያደርገው የሚለው ነው፡፡በራሳችን ግማሽ ሜዳ በጥልቀት ኳስን ካጣን አደገኛው ነገር ተቃራኒ ቡድን በፍጥነት በመልሶ ማጥቃት ሊጫወት ይችላል ፡፡ኳስን ላጣው ቡድን ጥሩ የመከላከል ሸግግር በተጫዋቾቹ ወደ መከላከል የሚደረግ ፈጣን ሽግግርን ያካትታል፡፡ይህም ሊሳካ የሚችለው ተጫዋቾቹ ኳስ ወደላይኛው የሜዳ ክፍል ሲሄድ ሊመለስ እንደሚችል በግምት መጠበቅ መቻላቸው ነው፡፡

ለዚህ ምሳሌው ኳስ ወደ መሀል ሜዳ ሲሄድ የመሀል ተከላካዮቹ እንዲያጠቡ ማድረግ ነው ወይም ኳሱ በተቃራኒው አቅጣጫ ሲሆን የመስመር ተከላካዩ (fullback) እንዲያጠብ ማድረግ ነው፡፡

ማጠቃለያ

ኳስ መስርቶ መጫወት በአግባቡ ሲሰራ ቡድን ኳስን ወደ ፊት በጥራትና መቆጣጠር በሚያችል መንገድ ይዞ መጠጋት እንዲችል ያስችላል፡፡በተጨማሪም ጠጋ ባለው የሜዳ ክፍል የቁጥር የበላይነት እንዲኖር ያስችላል፡፡በተለይም ቡድኑ በኳስ ምስረታው የተቃራኒ ቡድንን የመጀመሪያውን እና ሁለተኛውን የፕረሲንግ መስመር በጥሩ ሁኔታ ማስወገድ ከቻለ፡፡

በአብዛኛው ይህ አጨዋወት የተቃራኒ ቡድን መዋቅር ወደ አንድ አቅጣጫ ለማድረግ ሆን ብሎ ኳስን ብዙ ተጫዋቾች ወደአሉበት በመጫወትና በሌላኛው ሜዳ ጎን በጥሩ የኳስ ስርጭትና ኳስን በመገልበጥ መጠቀም ፡፡እንደውም ኳስ የያዘው ተከላካይ አጥቂው ፕረስ እስኪያደርገው መጠበቅ ይችላል ይህም ተቃራኒው ተጫዋች ፕረስ ሊያደርግ ሲመጣ የሚተወውን ክፍተት በመጠቀም ወደፊት ለማቀበል ያስችላል፡፡

ብዙ አሰልጣኞች የሚገጥማቸው የማይቀየር ፈተና በተፈለገው ፍጥነት እና አቅጣጫ ኳስን ማሰራጨት የሚችሉ ተጫዋቾችን አለመያዛቸው ነው፡፡በቡደን ስፓርት ክህሎትን ለማዳበር ሌላኛው አስፈላጊ ነገር በመመልክት መግባባት ነው፡፡

ምንም እንኳን ይህ በጣም ውስብስብ የሆነው እግር ኳስ አጭር ማብራሪያ ቢሆንም በጨዋታ ንድፋቸው ላይ ውጤታማ ኳስ ቁጥጥርን መተግበር ለሚፈለጉ ቡድኖች ከኋላ መስርቶ መጫወት በጣም አስቸጋሪ ነገር ግን በጣም የሚክስ መሆኑን እንደሚያስራዳ ተስፋ አለን፡፡


የጽሁፉ ተርጓሚ አሰልጣኝ ደስታ ታደሰ ነው፡፡ አሰልጣኙ ባለፉት አስር ዓመታት በበጎ ፍቃድ ታዳጊዎችን በማሰልጠንና ለበርካታ ክለቦች በማበርከት እውቅና ባተረፈው የአስኮ እግር ኳስ ፕሮጀክት ሲያሰለጥን ቆይቷል ፡፡ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ በአፍሮ-ፂዮን እግር ኳስ ክለብ ከ17 ዓመት በታች ቡድኑ አሰልጣኝ ሆኖ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡