በአዲስ አበባ ስታዲየም ብዙኀኑ የስፖርት ቤተሰብ እና አመራር የሚያቀው የቀድሞ ዳኛ እንዳልካቸው መኮንን (ሳንዱች) በከፍተኛ ችግር ውስጥ እንደሚገኝ ተናገረ።
በ1995 ወደ ዳኝነቱ እንደገባ የሚነገርለት እንዳልካቸው በዳኝነቱ ብዙም ሳይዘልቅበት ህመም አጋጥሞት ከዳኝነቱ ቢያቆምም ለዓመታት በአዲስ አበባ ስታዲየም የተለያዩ አገልግሎቶችን በመስጠት እና ጨዋታዎችን በመከታተል ይታወቃል። ቄራ አካባቢ ቤት ተከራይቶ ይኖር የነበረ ቢሆንም ቤቱ በልማት ምክንያት መፍረሱን ተከትሎ ወደ ጎዳና ለመውጣት ተገዷል።
በአሁኑ ወቅት አሮጌው ቄራ ውዳሴ ዲያግኖስቲክ አካባቢ የላስቲክ ቤት ውስጥ የሚኖረው እንዳልካቸው በተለይ በኮሮና ወረርሺኝ ምክንያት ወደ አዲስ አበባ ስታዲየም የማይመጣ መሆኑ ህይወት ለእርሱ ከባድ እንድትሆንበት እና ከፍተኛ ችግር ውስጥ እንዲገባ እንዳደረገው ለሶከር ኢትዮጵያ ተናግሯል። ” መጪው ክረምት ነው። ህመም አለብኝ፤ በዚህ ህመም ላይ የጎዳና ህይወት ተጨምሮ ጊዜው አስቸጋሪ እንዳይሆንብኝ የስፖርት ቤተሰቡ ድጋፍ እንዲያደርጉልኝ እጠይቃለው።” ብሏል።
ቀድሞ አብረው አብረውት ያገለገሉ ዳኞች ድጋፍ ለማድረግ እየተንቀሳቀሱ እንደሆኑ የሰማን ቢሆንም በዘላቂነት ከጎዳና ህይወት የሚወጣበት ድጋፍ እንዲደረግለት መልዕክታችን ነወ።
👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም
👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ
👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!
© ሶከር ኢትዮጵያ