በቅርቡ የተቋቋመው የትግራይ አሰልጣኞች ማሕበር በለይቶ ማቆያ ውስጥ ላሉ የጎዳና ተዳዳሪዎች ድጋፍ አደረገ።
በቅርቡ የተቋቋመው የትግራይ አሰልጣኞች ማኅበር በመቐለ ለይቶ ማቆያ ለተጠለሉት የጎዳና ተዳዳሪዎች የምግብ እና ሌሎች መሰረታዊ ፍላጎቶች ድጋፍ አደረገ።
ከስድስት ወራት በፊት የተመሰረተው ይህ ማኅበር ቀደም ብሎ ተመሳሳይ ድጋፍ ማድረጉ ሲታወስ አሁን ደግሞ በከተማው የሚገኙትን ባለ ሀብቶች አስተባብሮ ያሰባሰበው ገንዘብ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ህልውናቸው አስጊ ደረጃ ላይ ደርሶ ለነበሩት እና በአሁን ወቅት በለይቶ ማቆያ ውስጥ ለተጠለሉት በርካታ የጎዳና ተዳዳሪዎች ድጋፍ በማድረግ አጠናክሮ ቀጥሎታል።
ማኅበሩ በቀጣይ ጊዜያትም ተመሳሳይ ስራዎች እንደሚያከናውን ሲያስታውቅ በአሁኑ ሰዓትም ከተጠቀሰው ድጋፍ ውጭ በሳምንት ሦስት ቀን ሙያዊ ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ ማኅበሩ ገልፀዋል።
👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም
👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ
👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!
© ሶከር ኢትዮጵያ