የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋቾችን የሚያስታውስ መርሐ ግብር ተካሄደ

በኢትዮጵያ እግርኳስ ቀደምት እና መካከለኛው ዘመን በክለብ እና በብሔራዊ ቡድን ከፍተኛ ስም ያተረፉ የቀድሞ ተጫዋቾችን የሚዘክር መርሐግብር ተካሂዷል።

ከበደ መታፈሪያ (መቻል / በህይወት የሉም )፣ ጌታቸው አበበ (ዱላ) (ቅዱስ ጊዮርጊስ /በህይወት የሉም) እንዲሁም አበበ ጉርሙ(መቻል)፣ አቶ ዓለማየሁ ታደሰ (የቀድሞ የዳኘው ቡድን ተጫዋች እና ኦሜድላ አሰልጣኝ) ዓለም ንፀብኸ (የቀድሞ ዳኛ) በኢትዮጵያ እግርኳስ እና በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋፅኦ የእውቅና የምስጋና መርሐግብር በየሚኖሩበት መኖርያ ቤታቸው በመሄድ ስጦታውን አበርክተዋል።

ይህ የቀድሞ ባለውለተኞችን የሚያስበውን በጎ ተግባርን በማስተባበር ረገድ የቀድሞ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተጫዋች ሸዋረጋ ደስታ እና ጋዜጠኛ ታሪኬ ቀጭኔ ትልቁን ሚና ተወጥተዋል። የተለያዩ የምግብ እና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ድጋፍም አድርገዋል።

ጋዜጠኛ ታሪኬ ስለ ዛሬው በጎ ተግባር ውሎ “እነዚህ ሰዎች ለረዥም ዓመታት ክለባቸውን እና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንን በከፍተኛ ሁኔታ ያገለግሉ ባለውለተኛ ናቸው። ዛሬ ካደረግነው የቁሳቁስ ድጋፍ በላይ እነዚህን ባለ ውለተኞች ማስታወስ ነው ትልቁ ዓላማችን።” በማለት ተናግሯል።

ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ እግርኳስ ላይ አሻራቸውን ላሳረፉ 10 ለሚሆኑ ባለውለተኞች የተለያዩ የምግብ እና የንፅህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች ድጋፍ ማድረጋቸው ይታወቃል።

👉እጅዎን በተደጋጋሚ በሳሙና በአግባቡ በመታጠብ አልያም አልኮል እና ሳኒታይዘር በመጠቀም

👉ከሰዎች ጋር ንክኪ በማስወገድ

👉ከአላስፈላጊ እንቅስቃሴ በመገደብ፣ አካላዊ ርቀት በመጠበቅ እና በቤት በመቆየት ራሳችንን ከኮሮና ቫይረስ እንጠብቅ!


© ሶከር ኢትዮጵያ